+251118132191
contact@mint.gov.et
በዲጂታይዜሽን እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቀቀ፡፡
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት ዘላቂ የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለዋና መስሪያ ቤቱ እና ለተጠሪ ተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በዲጂታይዜሸንና በሠው ሠራሽ አስተውሎት ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።
በሥልጠናው መዝጊያ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽን ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ ለተሳታፊዎች የእውቅና ሠርተፍኬት ሰጥዋል፡፡
የእውቅና ሠርተፍኬቱን ከሰጡ በኃላ ያስተላለፉት መልዕክት ከተባበሩት መንግስታት ዘላቂ የልማት ፕሮግራም ጋር በዘርፉ በተለያዩ የልማት ፕሮግራሞች ባለፉት አምስት ዓመታት ሲሰራበት መቆየቱን ነው ያስታወሱት፡፡
አሁን የተሰጠው ሠልጠና የድርጅቱ የመጨረሻ ፕሮግራም መሆኑን ጠቁመው ለቀጣይ አምስት ዓመት የማስቀጠል ዓላማ መያዙን አንስተው በሥልጠናው ተሳታፊ ለነበሩ ሠልጣኞች በቆይታችሁ ያገኛችሁትን ክህሎትና እውቀት እየዘመነና እየተለዋወጠ ከሚሄደው የዓለም የቴክኖሎጂ ልቀት ጋር ተወዳዳሪ በመሆን እንድትራመዱ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
በዲጂታይዜሽን እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ልማት ዘርፍ እየተፈጠሩ ያሉ ቴክኖሎጂዎች እንግዳ ሳይሆኑ ራሳቸውን እያበቁ በቀጥታ የመጠቀምና የማስተዳደር ብሎም ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስፈልግ የክህሎትና እውቀት ክፍቶችን በመሙላት ለማሸጋገር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች