+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እንሰራለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ትልልቅ ሃሳቦች ያሏት፣ የራሷን ማንነት ገልጭ የሆነ እና እሴቶቿን የሚያንጸባርቅ ቴክኖሎጂ የምትጠቀም እንዲሁም አስፈላጊ ለሆኑ ፍላጎቶቻችን ምላሽ የሚሰጥ አሰራር ያላት ሀገር እንፈጥራለንም ብለዋል።

ይህንን እውን ለማድረግ የስማርት አሰራርን፥ ለኃይል መሠረተ ልማት፣ ለፈጣን ግንኙነት፣ ለመረጃ ቋት መፍጠር የመጀመሪያው እርምጃ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም የእድገት መሰረት ጠንካራ እና ዘላቂ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

በሁለተኛነት የዲጂታል ሉዓላዊነታችንን ለመጠበቅ የምንጠቅምባቸው ሲስተሞች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆን አለበት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። መረጃን በኃላፊነት በመመራት፤ ልማትን ማፋጠን እና ህዝባችንን ማብቃት ይኖርብናልም ሲሉ ተናግረዋል።

ዲጂታል የትምህርት ግብዓቶችን ማቅረብ እና የኤ.አይ ዘርፍ እውቀትን ወደ ትምህርት ቤቶች በማሻገር ተማሪዎችን ብቁ ማድረግም እንደሚጠይቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ዓላማችን ዜጎቻችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማብቃት ነው ያሉም ሲሆን፤ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ቴክኖሎጂ አቅም የሚሆነው በሚጠቀሙት ሰዎች አቅም ልክ በመሆኑ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በትልልቅ ከተሞችም ሆነ በጣም ሩቅ በሆነው የገጠር መንደር ተደራሽ የሚሆን ዲጂታል ኢኮኖሚን እውን ማድረግ፤ እንዲሁም ማንኛውም ሰው በራሱ ቋንቋ በስልኩ ብቻ መግዛት፣ መሸጥ፣ ክሬዲት ማግኘት እንዲችል ማድረግ፤ ህልማችንን ለማሳካት ሌላው ትልቁ እርምጃ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ