+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በSTI ፖሊሲ የማስፈጸሚያ ስትራቴጂ በርካታ ወሳኝ የትኩረት አቅጣጫዎችን አጽንኦት ተደርጎበቸዋል፡፡ ደ/ር ባይሳ በዳዳ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI) ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ስነድ ላይ ያተኮረ ወርክሾፕ አካሂዷል ።

በወርክሾፑ ማጠቃለያ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ድኤታ ደ/ር ባይሳ በዳዳ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI) ፖሊሲ ማስፈጸሚሚ ስትራቴጂ በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ስራዎችን በማስተባበር ላይ ለሚገኙ አካላት በእውቀት እና በፈጠራ ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ እድገትን ለማጎልበት የተነደፈ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ ሆኖ ያገለግላል ብለዋለል።

በSTI ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ በርካታ ወሳኝ የትኩረት አቅጣጫዎችን አጽንኦት ተደርጎበቸዋል ያሉት ሚኒስትር ድኤታው የፈጠራ ባህልን ማዳበር፣የምርምርና ልማት አቅሞችን ማስፋት፣ጠንካራ አጋርነትን መፍጠር እንዲሁም በኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ እድገታችን ውስጥ ማካተት እና በዘላቂነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ አንስተዋል።

በመድረኩ ላይ የተሳተፉ ሀላፊዎች ስትራቴጀው ተግባራዊ ሲደረግ የፌደራል እና የክልል ተቋማትን እንዲሁም የምርምር ተቋማትንና ዩንቨርሲቲዎችን ሊያሳትፍ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

የኢትዮያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ለአንድ ሃገር ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል ስትራቴጂው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ከማሳተፍ አንጻር ሊታይ እንደሚገባም አንስተዋል።

በተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል የፋናንስ ድጋፍ የተሰራው ይህ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ከቀጣዩ ጥር ወር ጀምሮ ወደ ስራ የሚገባ ሲሆን ለ10 አመት ተዘጋጅቶ በሶስት የአፈጻም የጊዜ ሰሌዳ የሚተገበር ነው፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ