+251118132191
contact@mint.gov.et
በSTRIDE 2024 ምርጥ የምርምርና ንግድ ሽልማት(Stride Award) ዘርፍ ሁለት የምርምር ውጤቶች ተሸልመዋል።
ከግንቦት 10 ጀምሮ በተካሄደው የስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ ላይ የተለያዩ ዝግጅቶች የተካሄዱ ሲሆን በዘርፉ የተሰሩ የምርምር እና የፈጠራ ስራዎችም ለውድድር ቀርበው አሸናፊዎቹ እውቅና ተበርክቶላቸዋል።
በSTRIDE 2024 ምርጥ የምርምርና ንግድ ሽልማት የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለመቀነስ የተሰራው የህክምና መሳርያ እና የእንሰት ማቀነባበሪያ ማሽኖች ተሸላሚ ሆነዋል።
የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለመቀነስ የተሰራው የህክምና መሳሪያ በአቶ ሃብታሙ አባፎጊ የተሰራ ሲሆን በጤና እና በሕክምና ምርምር የጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ የሚረዳ የህክምና መሳሪያ ነው።
አቶ ሃብታሙ አባፎጊ ይህንን መሳርያ በመስራት እና ወደ ገበያ በማስገባት በስትራይድ ሽልማት ምርጥ የምርምር ዘርፍ ተሸላሚ ሆነዋል።
በዚሁ ዘርፍ ዶ/ር አዲሱ ፍቃዱ የእንሰት ማቀነባበሪያ ማሽኖችን በተሳካ ሁኔታ በመገንባት እና ወደ ገበያ በማስገባት የምግብ ዋስትናን ለማሻሻል፣ የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን ለማሳደግ፣ የስራ እድል ለመፍጠር እና ዘላቂ ግብርናን ለማስተዋወቅ ባደረጉት ጥረት ተሸላሚ ሆነዋል።
በዝግጅቱ ላይ የፈጠራና የምርምር ባለሞያዎችን እውቅና መስጠት በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎችን እና ባለሞያዎችን ለማበረታታት እንደሚረዳ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ተናግረዋል።
በዚህ ፕሮግራም የተገኙት እና ሽልማቱን ያበረከቱት የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በስትራይድ ኢትዮጵያ ላይ የታዩት ተስፋ ሰጭ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በተለይም ወጣቶች እያደረጋችሁት ያለውን እንቅስቃሴ በራሳትሁ ጥረት መሆኑ ሊያኮራችሁ ይገባል ምንም እይነት ጎታች ሊያደናቅፋችሁ እንዳይሞክር መጠንከር ይገባችዋል እናንተ የኢትዮጵያ የወደፊት ተስፋዎች ናችውና ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለቴሌብር ሱፐርአፕ የተበረከተውን የምቹ ስነ ምህዳር ግንባታ ስትራይድ ሽልማትም ለተቋሙ ተወካይ አበርክተዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች