+251118132191
contact@mint.gov.et
ተረጂነት ኢትዮዽያን የማይመጥን ክብረ- ነክ ልምምድ በመሆኑ ሁሉም እራሱን ለመቻል ሀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተገለፀ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሠራተኞች “ከተረጂነት አስተሳሰብ መላቀቅ እና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ” በሚል በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ውይይት አካሄዱ።
በውይይቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ ያለትን እምቅ ሀብት ወደ ውጤት በመቀየር እርዳታ ተቀባይ ሳይሆን እርዳታ ሰጪ መሆን የሚያስችላት አቅም ለመፍጠር ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል።
ከልመናና የጠባቂነት ስሜት ለመላቀቅ ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ ውጤት ላይ የተመሰረተ ስራ መስራት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው እርዳታ የአንድን ሀገር ኢኮኖሚን ከማዳከም ባለፈ የሚፈጥረው አውንታዊ ጠቀሜታ እንደሌለ ሁሉም ዜጋ ሊያውቅ ይገባል ብለዋል።
ሀገራት በአጭር ጊዜ ያደጉት በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ላይ ተግተው በመስራታቸው መሆኑን አውቀን በዘርፉን ላይ ያለንን አቅም አሟጠን በመጠቀም ሀገራችንን ከተረጂነት ለማላቀቅ ሁሉም በተሰማራበት ዘርፍ መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በውይይቱ ላይ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፎዚያ አሚን ኢትዮጵያ ያሏት እምቅ የተፈጥሮ ጸጋዎች በአግባቡ ጥቅም ላይ ካዋለች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደማያዳግታት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ማሳያ መሆናቸውን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ባህል ያልሆነውን ተረጂነትን ለማስቀረት በሁሉም ዘርፎች ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የሀገራችንን ክብርና የታላቅነት ታሪክ አስከብሮ ለማቆየት ሁሉም በተሰማሩበት ዘርፍ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት የውይይቱ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች