+251118132191
contact@mint.gov.et
አለም ከደረሰበት የዲጅታላይዜሽንና የቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር እኩል ለመራመድ፣ የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅ ሚና ከፍተኛ ነው" --- የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ(ዶ/ር) -
(ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 4፣ 2017 ዓ.ም.፤ አዲስ አበባ፤ የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅ አለም ከደረሰበት የዲጅታላይዜሽንና የቴክኖሎጂ ዕድገት እኩል በመራመድ ሀገራችን በዲጅታል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንድትሆን እና ለወጣቶች ከፍተኛ የሆነ የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ(ዶ/ር) ገልጸዋል።
ይህ የተገለጸው በስታርታፕ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ቋሚ ኮሚቴው ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ የአስረጂ መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው።
በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር 70 በመቶው የሚሆነው በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኝ ይገመታል ያሉት ሰብሳቢው፣ ከዚህ አንፃር ረቂቅ አዋጁ በሚፀድቅበት ወቅት የተለያዩ የዕውቀት እና ተሰጥዖ ባለቤት የሆኑ ወጣቶችን ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም ካላቸው ሀገራዊና አለማቀፍ ባለሀብቶችና ድርጅቶች ጋር በማስተሳሰር ከፍተኛ የሆነ ሀብት እንዲፈጥሩ የሚያስችል ረቂቅ መሆኑን ሰብሳቢው ተናግረዋል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የሃገርን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት እና ለወጣቱ ከፍተኛ የስራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ አዳዲስ የሀብት ምንጮችን መሞከር እንደሚገባ ገልጸው፤ ረቂቁ በሚወጣበት ወቅት ሃሳብ ከማመንጨት እና አገልገሎት ማቅረብ የሚችሉ አካላትን በማስተሳሰር ምቹ የሆነ የኢኮኖሚ ስነ-ምህዳር መፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል።
አዋጁ ስታርታፕን ዒላማ ያደረገ ድጋፍን ለመስጠት የሚያስችል የተሳለጠ ሒደት እና ሥርዓት ለማስተዋወቅ፣ የስታርታፕ ምህዳርን ለማሳደግ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል፣ የግራንት ፕሮግራም፣ የብድር ዋስትና ማዕቀፍ እና የፈንዶች ፈንድ መዋቅርን ለማደራጀት ጠቃሚ እንደሆነ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በውይይቱ ወቅት በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ የትርጉም ግልፀኝነት፣ በአዋጁ መካተትና መቀነስ በሚገባቸው ፍሬ ነገሮች እንዲሁም በአዋጁ አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ዙሪያ ከቋሚ ኮሚቴው አባላትና የህግ ባለሙዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው በሚኒስቴሩ የስራ ሀላፊዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያና አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡
(በ ሚፍታህ ኪያር)
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች