+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፎች ኢትዮጵያ የማይቀለበስ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች ዶ/ር ባይሳ በዳዳ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ አመራሮችና ሠራተኖች ባለፉት 7 ዓመታት በለውጡ መንግስት በተሰሩ ስራዎች የተገኙ ስኬቶች ላይ ‘ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!’ በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሂደዋል፡፡

በለውጡ ዓመታት የተገኙ ድሎችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም አጠቃላይ በኢኮኖሚውና በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ባለፉት ሰባት የለውጥ አመታት እንደ ሀገር በርካታ ውጤቶችና ስኬቶች የተመዘገቡበት እንደሆነ ጠቅሰው በተለይም ከለውጡ በፊት በአገራችን ላይ የተጋረጠውን የመበታተን አደጋና ስጋት ተቀርፎ ወደ ላቀ ብልጽግና የተሸጋገርንበትን መሰረት የጣለው ሁነት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የተደረገበት ቀን ነው ብዋል፡፡

ባለፉት 7 የለውጥ ዓመታት ውስጥ የሀገራችንን ፀጋዎች ስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ብዝሃ-ዘርፍ የኢኮኖሚ አቅምን በመሸለም በተለይም በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የተመራ የኢኮኖሚ ስትራቴጂ በመንደፍ በለተግባራዊነቱ ርብርብ መደረጉን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፎች በተለይም በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ መሰረት የተጣለበት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ትልቅ ድል የተመዘገበበት ሲሆን በስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራና በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮች የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ መቻሉን፣ አገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙን በዲጂታላይዜሸን ጭምር መምራት መቻሉን፣ ኢኖቬሽን ልማትንና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን ለኢንተር ፕርነርሽፕና ሀብት ፈጠራ መነሻ ያደረገ የኢኮኖሚ አማራጭ እንዲጣል መሰረት የተጣለበት የለውጥ ዘመን ነው ብለዋል፡፡

በኢኖቬሽን ልማት ዘርፍ በተለይም ከተሞቻችንን የስታርታፕ ከተሞች በማድረግ የመጣው ለውጥ ለወደፊት መሰረት የሚጥልና ብዙ የታሪክ እጥፋቶችን ያመጣንበት መሆኑን አውስተው የተገኘውን ድል ለማጽናትና ለማስቀጠል አመራሩና ሰራተኛው በበለጠ ቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የለውጡ ዓመታት በኢኮኖሚው ዘርፍ በግብርና ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ የቆየውን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብዝሃ-ዘርፍ ኢኮኖሚ በማድረግ ከግብርናው ባለፈ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝምና በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ዘርፎች ላይ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑም ከተሳታፊዎች ጭምር በአጽንኦት ተብራርቷል።

የለውጡ ባለቤቶች እኛው ነን ያሉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ለውጡን ለማጽናት ለማስቀጠልና ኢትዮጵያን በዲጂታል ቴክኖሎጂና ኢኮኖሚ ቀዳሚ ተጠቃሽ አገር ለማድረግ ልንረባረብ ይገባል ብለዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ