+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮዽያ በአልጀሪስ እየተከሄደ ባለው 3ኛው የአፍሪካ ስታርታፕ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው።

በአልጀሪያ አልጀርስ ከተማ 3ኛው የአፍሪካ ስታርታፕ ጉባኤ (African Startup Conference) እና አውደ-ርዕይ ተከፈተ።

በጉባኤው 4 የኢትዮጵያ ስታርታፖችን ያሳተፈ ሲሆን ከተለይዩ የአፍሪካና ሌሎች ሀገራት ከ350 በላይ ኤክስፐርቶች፣ 300 በላይ ኢንቨስተሮች፣ 45 የአፍሪካ ኢኖቬሽን ሚኒስትሮች፣ ከ25000 በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት ኢትዮጵያ የጉባኤው የክብር ዕንግዳ ሆና ተወክላለች።

ኮንፈረንሱን የአልጄሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር የከፈቱት ሲሆን፤ በዚህ ኮንፈረንስ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የጉባኤው የክብር ዕንግድነትን ወክለው በጉባኤው መክፈቻ ላይ አፍሪካ በኢኖቬሽን ላይ የተመሰረተ ለውጥ ለማምጣት ያላትን ፍላጎት የሚያሳይ እና የአፍሪካን የኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በዲጂታል ፋይናንስ፣ በናሽናል አይዲ፣ በቴሌኮም እና ምቹ የስታርታፕ ስነ-ምህዳር በመፍጠር መጠነ ሰፊ ተግባራትን በማከናውን ላይ ትገኛለች ብለዋል።

አክለውም "Reimagine Africa with AI" አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እንደ ረቂቅ ፅንሰ ሀሳብ ሳይሆን እንደ ማደጊያ መሳሪያ ሆኖ ለግብርና፣ ለጤና፣ ለትምህርት እና አስተዳደር ያሉ ዘርፎችን የመቀየር አቅም እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

3ኛው የአፍሪካ ስታርታፕ ጉባኤ እና አውደ-ርዕይ የአፍሪካ ስታርታፕ ከ2025 እስከ 2063 የትግበራ ዕቅድ፣ በኢትዮጵያ የቻምበር ኦፍ ኮሜርስ ተወካይ ፓናል፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ ያተኮሩ ፓናል የሀገራት የሚኒስትሮች ውይይቶችና፣ የአፍሪካ ስታርታፕ ጉባኤ ዲክላሬሽን እና አውደ-ርዕዩ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ