+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያና ህንድ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መከሩ

የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር እና የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ የሆኑት ክቡር አኒል ኩማር ራይ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ላይ በጋራ ለመስራት መክረዋል፡፡

ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በአምባሳደር አኒል ኩማር ራይ በኩል ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የተላከላቸውን ስጦታ በመቀበል ለተበረከተላቸው ስጦታ በማመስገን ለህንደ የገና በዓል እምነት ተከታዮችና ለመጪው የፈረንጆች አዲስ አመት እንኳን አደረሳችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ካስመዘገበቻቸው ስኬቶች የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ላይ በትብብር ከአጋር አካላት ጋር ለመስራት ትኩረት የሰጡበት ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያና ህንድ የረጅም ጊዜ የጠበቀ የባህል ትስስር ያላቸው ሀገራት ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ ሀገራችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሰፊ ልምድና አቅም ካላት ከህንድ ጋር አብራ ለመስራት አብዝታ የምትሻው በመሆኑ አዳዲስ እድሎችን ለመፍጠር ትብብሩ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ስኬታማ ከመሆኑም ባለፈ ለአፍሪካ ትልቅ ልምድ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ላይ የህንድ መንግስትና ኢንቬስተሮች በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳላቸውና የተጀመሩትን በስፔስ፣ በባዮ-ቴክኖሎጂ፣ በኒኩለር፣ በአይሲቲና በሌሎች ዘርፎች ላይ ያሉትን አጋርነት አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግኑኝነት በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በትብብር ስራዎች ላይ በመምከር ህንድ በምታዘጋጀው የቴክኖሎጂ አውደርዕይ ላይ ዶ/ር በለጠ ሞላ እንዲገኙ ግብዣ ቀርቦላቸዋል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ