+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያና ሩሲያ በዘርፈ ብዙ መስኮች ላይ የሚሰሯቸውን የትብብር ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሩሲያ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ምክትል ሚንስትር ኤች ኮንስታንቲን ሞጊሌቭስኪ ከተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ውይይቱ በርካታ የሁለትዮሽ ጉዳዮችን የዳሰሰ ሲሆን የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትብብርን በተመለከተ፣ የኢትዮጵያና ሩሲያ የጋራ የባዮሎጂካል ምርምር ማዕከልን እውን ስለማድረግ፣ በሩስያ ዩንቨርሲቲዎች በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሰው ሃብት ልማትን እንዲሁም የሩሲያ ቋንቋን በኢትዮጵያ ለማስተማር ባለው ፍላጎት ላይ ያተኮረ ነበር።

በውይይቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፤ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ረጅም የወዳጅነት ዘመን ገልጸው ፤ሀገራቱ ያላቸውን እምቅ አቅም በማስታወስ አሁንም በስፋት ሊሰሩ የሚገባቸው በርካታ እድሎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

የሩሲያ ልዑክ የኢትዮጵያና ሩሲያ የጋራ የባዮሎጂካል ምርምር ማዕከል በኢትዮጵያ ለማቋቋም የተጀመረው ጥረት ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ አጋዥ ነው በማለት ስምምነቱ ወደ ተግባር እንዲለወጥ አንስተዋል።

ለዚህም በጉዳዩ ዙርያ በትኩረት ይሰራል ያሉት ሚኒስትሩ የሰው ሃይል ልማትን በተመለከት ሩስያ ለሀገራችን የምታደርገው ድጋፍ እንደሚያደንቁ ጠቁመው ይሄው ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ገልጸዋል።

በሩስያና እትዮጵያ ትብብር የሚቋቋመው የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከሮሳቶም ጋር በጥሩ የመግባባት መንፈስ እየሰሩ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ባጭር ጊዜ የመጨረሻውን የአዋጭነት ጥናት ስምምነት ሰነድ እንደሚፈርሙ አብራርተዋል።

ማዕከሉ የኒውክሌር ምርምርን ከማከናወን ባለፈ ለተለያዩ ዘርፎች ግብዓት በማቅረብ ለኒውክሌር ታዳሽ ሃይል አቅርቦትም መደላድል የሚጥል መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የሩሲያ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ምክትል ሚንስትር ኤች ኮንስታንቲን ሞጊሌቭስኪ በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገውን ግንኙነት በተለያዩ መስኮች አጠናክራ የመቀጠል ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።

ክቡር ምክትል ሚኒስትሩ በሰው ሃብት ልማት ከመላው አፍሪካ ከ35ሺ በላይ ተማሪዎች በሩስያ በመማር ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በሩስያ እንዲማሩ ሀገራቸው አስፈላጊውን ሁሉ እንደምታደርግም ተናግረዋል።

በተለይም የኢትዮጵያና ሩሲያ የጋራ የባዮሎጂካል ምርምር ማዕከል እና የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከሉ ሲቋቋም የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ የሁለቱ ሀገራት ሙህራን በእነዚህ ማዕከላት ልምዳቸውን እንዲያዳብሩ እንደሚያግዝም እንስተዋል።

በውይይቱ በቀጣይ የመግባቢያ ስምምነት በመፈረም ወደ ስራ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ