+251118132191
contact@mint.gov.et
ኢትዮጵያና አልጄሪያ በምርምር፣ በልማትና በስታርታፕ ዘርፎች በጋራ ለመስራት መከሩ፡፡
የኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና አልጄሪያ የእውቀት ኢኮኖሚ፣ ስታርታፕ እና የጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ሚኒስቴር በምርምር፣ በልማትና በስታርታፕ ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት መክረዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የምርምር፣ የልማትና የስታርታፕ ዘርፉን ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገትና ለዘላቂ ልማት ለማዋል በስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ በትኩረት እየሰራችና ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች ብለዋል።
ሀገራችን የአፍሪካ ተምሳሌት ለመሆን ለቴክኖሎጂው ዘርፍ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ላይ መሆኗን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን በስኬት በማጠናቀቅና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን በላቀ ሁኔታ በመፈፀም በዓለም ተወዳዳሪ ለመሆን እየተጋች መሆኗን አመላክተዋል።
ኢትዮጵያ የጀመረችውን የቴክኖሎጂ እድገት ለማፋጠንና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን ለማረጋገጥ፣ እንደ አልጄሪያ ካሉ ልምድ ካላቸው አጋር ሀገራት ጋር በቅርበትና በትብብር ለመስራት ሁሌም ዝግጁ መሆኗ ገልፀዋል፡፡
የአልጄሪያ የእውቀት ኢኮኖሚ፣ ስታርታፕ እና የጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ሚኒስትር ኑሬዲን ኦውዳህ (Noureddine Ouadah) በበኩላቸው፤ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የምርምር፣ የልማትና የስታርታፕ ዘርፍን ለማጎልበት የሚያስችል የጋራ ማዕቀፍ በማዘጋጀት በስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ ለመስራት ፅኑ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በዘርፉ ትልቅ አቅም እንዳላት ማስተዋል እንደቻሉ የገለፁት ሚኒስትሩ፤ አልጄሪያ ቀደም ሲል የስታርታፕ ኮንፍረንስ በምታዘጋጅበት ወቅት ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንደነበረች አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ አህጉራዊ ኮንፍረንሶችን የማዘጋጀት ልምድ ያላት ሀገር በመሆኗ በቀጣይ የስታርታፕ መድረኮችን ማዘጋጀት እንዳለባትም ጠቁመዋል።
በመጨረሻም ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ በጋራ ለመስራት በመስማማት፣ ስምምነቱን በፍጥነት ወደ ስራ ለማስገባት ከሁለቱም ወገን ኃላፊነት ወስደው የሚያስተባብሩ ኮሚቴዎችን በቀጣይ እንደሚሰይሙ ተስማምተዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች