+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያን ለንግድ ስራ ምቹ እንድትሆን ለማስቻል የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የንግድ ፖርታል የተጠቃሚ ግብአት ማሰባሰብያ እና ሲስተም ፍተሻ መርሀግብር በማካሄድ ላይ ነው።

ሀሳቡ በክቡር የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የተጠነሰሰ ሲሆን የቢዝነስ ፖርታሉ አላማ የተመረጡ የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላየን አማካኝነት ተደራሽ ማድረግ፣ ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት የሚያወጡትን ወጪ እና ግዜ በመቀነስ የንግድ ስራን ቀልጣፋ ማድረግ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ ኢትዮጵያን ለንግድ ስራ ምቹ እንድትሆን ለማስቻል የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያን የንግድ ምኅዳሩን እና ሁኔታ በማሻሻል ለንግድ ስራ እና ኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ አንድ ወጥ የሆነው የብሄራዊ የንግድ ፖርታል በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ ለምቶ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሉ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ቢሮዎች አስቀድሞ ወደ ስራ መግባቱንም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።

ሚኒስትር ድኤታው እያይዘውም አገልግሎቱን ወደ ክልል ከተሞች ለማስፋፋት የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸው ኢትዮጵያን የአለም የንግድ ድርጅት አባል ለማድረግ የንግድ ስራዎችን የሚያቀሉ አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የስራ ቅልጠፍና ለማምጣት በአለም ባንክ ከተለዩት 10 ጠቋሚዎች መካከል በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር "ንግድ ለመጀመር"፣ በገቢዎች ሚኒስቴር "ግብር ለመክፈል" በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት “መብራት ለማግኘት” እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድን እና ቁጥጥር ባለስልጣን "ግንባታ ፍቃድ ለማግኘት" ጥቂቶቹ ሲሆኑ እነዚህን ጠቋሚዎች መሰረት በማድረግ የተለዩትን አገልግሎቶች ዲጂታይዝ የተደረጉና በሂደት ላይ የሚገኙም አሉ።

የከተሞች የግንባታ ፍቃድ አገልግሎትን በባህርዳር፣ድሬድዋ እና አዳማ ከተማ የፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀግብር አስቀድሞ የተከናወነ ሲሆን የከተሞቹን የግንባታ ፍቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት እና ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ በኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካኝነት የንግድ ፖርታሉ ለምቷል።

በቀጣይም ፖርታሉ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት የለማው ፖርታል በተሰበሰበው የልማት ፍላጎት መሰረት መሆኑን ለማረጋገጥ እና ፍተሻ ለማድረግ ከከተሞቹ ለመጡ የግንባታ ፍቃድ እና ኢ.ኮቴ ባለሞያዎች የማረጋገጫ እና ፍተሸ መርኀግብር እየተከናወነ ይገኛል።

በሚሰበሰበው ግብዓት ተመስርቶ ማስተካከያዎች በማድረግ በቀጣይ ከከተማ አስተዳደሮቹ ጋር በመተባበር ወደ ስራ ይገባል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ