+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በቴክኖሎጂና በፈጠራ ተወዳዳሪ ሆነው ሀገራቸውን ማስጠራት ጀምረዋል።ዶ/ር ባይሳ በዳዳ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ የትምህርትና ውድድር ማእከል ጋር በመተባበር በ ENJOY AI Competition ሮቦቲክስ ስልጠና ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ተማሪዎች የሰርቴፊኬትና የእውቅና መስጠት መርሀ ግብር አካሄደ።

በፕሮግራሙ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ መንግስት ወጣቶች እና ህፃናት ያላቸውን ተሰጥኦ እንዲያወጡ እና ሀገራችን የምታደርገውን የቴክኖሎጂ እና ዲጂታላይዜሽን ጉዞ ዋና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ ምቹ ስነምህዳር ፈጥሮ ወጣቶች የማበረታታትና የመደገፍ ስራ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት መንግስት በወጣቶች ላይ የሰራው ሰፊ የማበረታታትና የመደገፍ ተግባር ውጤት አፍርቶ ወጣቶች በተለያዩ አለማት በቴክኖሎጂና በፈጠራ ተወዳዳሪ ሆነው ሀገራቸውን ማስጠራት ጀምረዋል ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ይሀንን ውጤት ለማጠናከር መንግስት ብቻውን ሳይሆን እንደ ኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ ከመሳሰሉት የግል ድርጅቶች በቅንጅትና በትብብር መስራት ይፈልጋል ብለዋል፡፡

ኢትዮ ሮቦ ሮቦቲከስ የትምህርትና የስልጠና ማእከል ወጣተቶች እና ህፃናት በሂሳብ፣ በሳይንስ፣በቴከኖሎጂ እና በኢንጅነሪንግ ስልጠና የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡

ህፃናቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ የስልጠና ማዕከል በመተባበር በሮቦቲከስ ፕሮግራሚንግ እና ኢንጅነሪንግ በማሰልጠን በቻይና ሀገር በተካሄደው (World Global ENJOY AI Competition) ውድድር ላይ በመሳተፍ በGalactic Defence Battle competition የሶስተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ የሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ የሆኑ ናቸው፡፡

የኢትዮ ሮቦ ሮበቲክስ መስራችና ዋና ስራ አስከያጅ ሰናክሪም መኮነን ኢትዮ ሮቦ ሮቦቲክስ በቴክኖሎጂ የዳበረ እውቀት ያላቸውና ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ ወጣቶች ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ በመሆናቸው እነዚህ ወጣቶች የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ አተገባበርን በመማር ሮቦትን እንዲቀርጹ፣ ሮቦትን ኮዲንግ እንዲያደርጉ እና ፕሮግራም እንዲያዘጋጁ የሚያስችል ስልጠና ይሰጣል ብለዋል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ