+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይና ውጭ የሚካሄደውን ግዙፉን የዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ኮንፈረንስ (WIC) በአዲስ አበባ ለማዘጋጀት ዝግጅት እያደረገች መሆኑ ተገለጸ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ የዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ኮንፈረንስ (WIC) ምክትል ዋና ፀሐፊ ሚስተር ሊያን ሃኦን (Mr. Lian Hao) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ኮንፈረንስ ዙሪያ መክረዋል።

ምክክሩ በመጪው መስከረም ወር በአዲስ አበባ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ኮንፈረንስ በስኬት እንዲጠናቀቅ በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችና ሂደቶች ላይ ያተኮረ ነበር።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን በብቃት የማስተናገድ ልምድ ያላት በመሆኑ፣ ይህንኑ ተጨማሪ ዕድል ተጠቅማ ለኮንፈረንሱ ስኬታማነት አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

ለኮንፈረንሱ ስኬት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ መድረኩ ኢትዮጵያን ተመራጭ የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ከማድረግ አንጻር ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ አስገንዝበዋል።

የዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ኮንፈረንስ የWIC ዋና ምክትል ዋና ፀሐፊ ሚስተር ሊያን ሃኦን (Mr. Lian Hao) ኮንፈረንሱን በአዲስ አበባ ለማካሄድ የሚያስችሉ የቴክኒክ ሥራዎች መጀመራቸውንና በቅርቡም በቅድመ ዝግጅቱ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በትብብር እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ከ2012 ጀምሮ በየዓመቱ በቻይና ሲካሄድ የቆየው ይህ ኮንፈረንስ፣ እንደ ጎግል፣ አይ.ቢ.ኤም (IBM)፣ ኒቪዲያ (NVIDIA) እና አሊባባ ያሉ ከ200 በላይ ግዙፍ የዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማትን በአባልነት የያዘ ትልቅ መድረክ ነው።

በመድረኩ የዓለም አቀፍ የዘርፉ ተዋናዮች፣ ምሁራንና ከፍተኛ የሀገራት ባለሥልጣናት የሚሳተፉበት በመሆኑ፣ ለኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ለኢንቨስትመንት መስፋፋት አዲስ በር እንደሚከፍት ይጠበቃል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ