+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ ለአርቲፊሻል ኢንተጀንስ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራች ትገኛለች። ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ

13ኛው የአፍሪካ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባዔ “Building our Multistakeholder Digital Future” በሚል መሪቃል በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በፎረሙ ሁለተኛ ቀን ውሎ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የአፍሪካ ዲጂታል ንግድ ፕሮቶኮልን ከአፍሪካ ዳታ ፍትህ አጀንዳ ጋር ማጣጣም፣የበይነመረብ አስተዳደር፣ በወጣቶች የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን መምራት፣ በአፍሪካ ውስጥ የስርዓተ-ፆታ ምላሽ፣ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣ የሳይበር ወንጀል እና አካታች የበይነመረብ ዙርያ ውይይቶች ተካሂዷል።

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘመን በአፍሪካ ውስጥ ዲጂታል ማካተት ያለበት ሁኔታ፣ ተግዳሮቶች እና የወደፊት ዕይታዎች በሚል ርዕስ በተካሄደው ውይይት ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ተሳትፈዋል።

በውይይቱ ኢትዮጵያ ለአርቲፊሻል ኢንተጀንስ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራች መሆኗን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው አፍሪካዊያን ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በቂ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎች ሚና ላይ በማተኮር በአፍሪካ ውስጥ ያለውን የዲጂታል ማካተት ሁኔታ ለመገምገም፣ በAI-ተኮር ቴክኖሎጂዎች ፍትሃዊ ተደራሽነትን የማረጋገጥ ቁልፍ ተግዳሮቶችን ለመዳሰስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በሀገራችን ኢትዮጵያ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ከጅምሩ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታችና ተስፋሰጪ በመሆናቸው የበለጠ አጠናክረን በትኩረት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

መሠረተ ልማት፣ ተመጣጣኝ አቅም እንዲሁም ዲጂታል ክህሎትን ጨምሮ በAI-የተዘጋጁ ቴክኖሎጂዎች ፍትሃዊ ተደራሽነትን የማረጋገጥ ቁልፍ ተግዳሮቶችን በተመለከተ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ሀገራት ተወካዮች ተሞክሮዎቻቸው አቅርበዋል።

ትምህርትን፣ ጤናን፣ ግብርና እና ፋይናንስን ጨምሮ አንዳንድ የአፍሪካን ልዩ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በAI እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ለማጉላት ሰፊ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅ ተነስቷል።

በAI እና ዲጂታል ማካተት የወደፊት አዝማሚያዎችን እና እድሎችን ለመለየት እና ለአካታች አርቲፊሻል ኢንተለጀንት አስተዳደር የፖሊሲ ምክሮች፣ በውይይት የተነሱ ተዛማጅ ጉዳዮች ግብአት እንደሚሆኑ ተጠቅሷል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ