+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ መስራች አባል የሆነችበት የአለም የአርተፊሻል ኢንተሊጀንስ የትብብር ድርጅት (World Artificial Intelligence Cooperation Organization -- WAICO) ተመሠረተ።

የ 2026 የአለም የአርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ኮንፈረንስ በቻይና ሻንጋይ ከተማ ሲካሄድ ኢትዮጵያን በመወከል በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የተመራ የልኡካን ቡድን በኮንፍረንሱ ላይ ተሳትፏል። ኮንፍረንሱን በንግግር የከፈቱት የህዝባዊ ቻይና ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ክቡር ሺ ጂን ፒንግ "የአርተፊሻል ኢንተልጀንስ እድገት የትኛውንም አገር ደህንነት ሳይነካና ሳያበላልጥ ለልማት መዋል እና ለሠው ልጆች ብልጽግና እና እድገት መዋል አለበት ፣ ይህም እንዲሳካ ቻይና አበክራ ትሰራለች" ብለዋል ።

በስብሰባው መክፈቻ ላይ የተገኙት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በበኩላቸው "አርተፊሻል ኢንተለጀንስን ለልማት በማዋል ሂደት ከሁሉም በላይ የጋራ ብልጽግና እና ደህንነት ቅድሚያ ሊሠጠው ይገባል ብለዋል።

በዚሁ ኮንፈረንስ ላይ የአለም አርተፊሻል ኢንተለጀንስ የትብብር ተቋም (World Artificial Intelligence Cooperation Organization -- WAICO) ኢትዮጵያን ጨምሮ በ29 አገራት ስምምነት ተመስርቷል። ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያን በመወከል የተቋሙ የምስረታ ስምምነት ሰነድን ፈርመዋል። በምስረታው ቅድመ ውይይት ላይ ንግግር ያደረጉት ክቡር ሚንስትሩ ኢትዮጵያ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ለአገር እድገት እና ደህንነት ያለውን ፋይዳ ቀደም ብላ በመገንዘብ በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የአርተፊሻል ኢንተልጀንስ ተቋም በማቋቋም እና የአርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ፖሊሲ በመንደፍ ወደ ተጨባጭ ስራ መግባቷን አብራርተዋል።

ሚንስትሩ ጨምረውም ኢትዮጵያ ከሌሎች ለመማር እና ልምዷን ለማካፈል በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠው አሁን የተመሠረተውና በርካታ አገራትን ያሳተፈው ድርጅት ሃላፊነት ለተሞላበት እና ፍትሃዊ አለም አቀፍ የአርተፊሻል ኢንተልጀንስ ልማት አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረው ቻይና ይህ ተቋም እንዲመሠረትም ሆነ ቴክኖሎጂው እንዲስፋፋ ለኢትዮጵያ ጨምሮ ለታዳጊ አገራት ለምታደርገው ጥረት አመስግነዋል።

የተመሰረተውንም ተቋም በተመለከተ ፕሬዚደንት ሺ ጂን ፒንግ ሲናገሩ "በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ልማት ላይ የሚሰራ የመጀመሪያው የበይነ መንግስታት ተቋም መሆኑን በመግለጽ ተቋሙ ለአለም አቀፍ የአርተፊሻል ኢንተልጀንስ አስተዳደር እና የጋራ ልማት መሠረት ይጥላል ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ቻይና በዚሁ ማእቀፍ በሚቀጥሉት 5 አመታት 5000 ስልጠናዎችን እንደምትሠጥ፣ ኦፕን ሶርስ ሞዴሎችን ከአገራት ጋር በመተባበር እንደምታለማ፣ የአተፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረተ ልማት ላይ በሚደረጉ የቅንጅት ኢንቨስትመንቶች ላይ እንደምትሳተፍ ፣ የቅንጅት አፕሊኬሽን እና አገልግሎት ልማትን እንደሞትደግፍ እና ባጠቃላይም በዘርፉ ያላትን እውቀት ለማካፈል እና አብሮ ለመስራት የአርተፊሻል ኢንተሊጀንስ የትብብር ማእከል እንደምትከፍት አስታውቀዋል ።

በኮንፍረንሱ ላይ የአገራት መሪዎች ፣ ከፍተኛ ሃላፊዎች ፣ የዘርፉ ከፍተኛ ተመራማሪ ሳይንቲስቶች፣ እና የአለም አቀፍ ድርጅቶች ተገኝተዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ