+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ የሚመረት የኢነርጂ መፍትሔን ለማረጋገጥ እየሠራች መሆኑ ተገለጸ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይና ደቡባዊ ግሪድ ቴክኖሎጂ እና ከኢዳን ፓወር ቡድን ጋር በመተባበር የኢነርጂ መፍትሄዎችን ከውጭ የማስገባት ጥገኝነትን በማስቀረት በሀገር ውስጥ ወደ ማምረት የሚያሸጋግር አዲስ ምዕራፍ (Paradigm Shift Toward "Made in Ethiopia" Energy Solutions and Tech Localization) መጀመሩ ይፋ አደረገ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ለቴክኖሎጂ ዕድገት መሰረት በመሆኑ፣ የአገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ከግብ ለማድረስ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት መገንባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

በቻይና ሳውዘርን ግሪድ ቴክኖሎጂ (China Southern Power Grid) እና በኤዳን ፓወር ግሩፕ (EDAN Power Group) መካከል የተመሰረተው አጋርነት፤ ኢትዮጵያ ዘመናዊ የኃይል መፍትሔዎችን በራሷ አቅም እንድታመርትና የኃይል ሉዓላዊነቷን እንድታጠናክር የሚያስችል ስትራቴጂካዊ እርምጃ መሆኑን አመላክተዋል።

የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በዘላቂነት ለማሟላት ከዋናው የኃይል መስመር በተጨማሪ አነስተኛ የኃይል መረቦች (mini-grids) እና ታዳሽ የኃይል ምንጮችን ማቀናጀት በየአካባቢው ለሚገኙ የሥራ ፈጣሪዎች ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የኤዳን ኤሌክትሮ ፓወር ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ እድሪስ አደም፤ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ ላይ የተመሠረተው ስልታዊ ትብብር የቴክኖሎጂ ሽግግርንና ዲጂታላይዜሽንን በማፋጠን፣ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትንና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማጎልበት የሀገሪቱን የኢነርጂ ዋስትና ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ገልፀዋል።

የቻይና ሳውዘርን ፓወር ግሪድ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ከፍተኛ ተወካይ ዣኦ ዚዪ፤ በኢትዮጵያ የኃይል ዘርፍ በሚከናወኑ የዘመናዊ ግሪድና የኃይል ማከማቻ (Storage) ቴክኖሎጂዎች ላይ በትብብር ለመስራትና የሀገሪቱን ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በመጨረሻም በኢትዮጵያና በቻይና መካከል የተመሰረተው የኢነርጂ ስምምነት የቴክኖሎጂ ሽግግሮችን እና የሰው ሃይል ሥልጠና ፕሮግራሞችን የሚያበረታታ በመሆኑ እና ዘላቂነትን የሚያረጋግጥ ስለሆነ ለተግባራዊነቱም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ ተገልጿል።

የሃገር በቀል የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ከሌሎች ሃገራት መሰል ኩባንያዎች ጋር አብረው እንዲሰሩ፣ ቴክኖሎጂን እንዲማሩና እንዲያሸጋግሩ ሁኔታዎችን በመፍጠር አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ