+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ላይ ተጽእኖ በሚያሳድር የዲጂታል የለውጥ ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ ገለፁ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 2ኛውን የኢትዮጵያ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ የዘርፉ ተዋናዮች በተገኙበት አካሂዷል።

በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የማይበገር እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሳይበር ምህዳር ለመፍጠር በመንግስት እና በግሉ ሴክተሮች እንዲሁም በአለም አቀፍ አጋርነት መካከል ያለው ትብብር ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል።

የዲጂታል ዘርፉ ሁሉን አሳታፊ ፣ ጤነኛ እና ዘላቂ እድገት እንዲኖረው የሚያስችሉ በርካታ የህግ ማዕቀፎች እንዲወጡ እና ስራ ላይ እንዲውሉ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የወደፊታችንን አሃዛዊ ቅርፅ እየቀረፅን ስንሄድ ፈጠራን የሚያበረታቱ፣ የግለሰብ መብቶችን የሚያስጠብቁ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በሁሉም ዘርፎች እና ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራታችን እና የዲጂታል አብዮቱ ጥቅሞች ሁሉም የሚጋሩት መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

በዝግጅቱ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ የኢትዮ ቴሌኮሙኒኬሽን ዋና የቴክኖሎጂ ኦፊሰር አቶ ታሪኩ ደምሴ የኢትዮጵያን ዲጂታል አቅም ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና በዲጂታል ክህሎት ላይ አየተሰራ መሆኑን ገለፀዋል።

ለኢትዮጵያ ስኬታማ የዲጂታል መፃኢ ጉዞዎች እርስ በርስ የተሳሰሩ የመረጃ አስተዳደር፣ የሳይበር ደህንነት፣ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የዲጂታል መብቶች እና ሁለንተናዊ የተደራሽነት ጉዳዮችን የሚፈታ የተቀናጀ እና ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂ ላይ መሰራት እንዳለበት ተሳታፊዎች አንስተዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ