+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የኢኖቬሽን ኢንዴክስ ያላትን ደረጃ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተዋቀረ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ደረጃ ለማሳደግ ከ2020- 2024 ዓ.ም በኢትዮጵያ የአለም አቀፍ ኢንዴክስ ሪፖርት ላይ ጥናት በማካሄድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መክረዋል፡፡

መድረኩ የግሎባል ኢኖቬሽን ኢንዴክስ ደረጃን ለማሳደግ በሚያስችሉ ዘርፎች ላይ የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ኢትዮጵያ ያለችበትን ደረጃ ለማሻሻል ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እንደ ሀገር የምናከናውናቸው ተግባራት እና ያሉን እምቅ ሀብቶች በአግባቡ በማጥናትና በማደራጀት መረጃ ለሚፈልጉ አለማቀፍ ድርጅቶች በመስጠት የሀገራችን ገፅታ መገንባት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ሀገራዊ ስራዎቻችንን ዲጂታላይዝ በማድረግ የሁለም ተቋማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የግንዛቤ መድረኮችን በመፍጠር ያሉንን የመረጃ ሀብት ማግኘትና መጠቀም የምንችልበት ስርዓት መፈጠር እንዳለበት ተናግረዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ በአለማቀፍ ኢኖቬሽን ኢንዴክስ ያላትን ደረጃ ወደ ውጭ ከምንልካቸው ምርቶች የሚፈለገውን ገቢ ለማግኘት እና በኢትዮጵያ ኢንቨስት በሚያደርጉ አካላት ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር ሁሉም በዘርፉ ላይ በትብብር መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የአለምአቀፍ ኢኖቬሽን ኢንዴክስ ሪፖርት ትኩረቱን በተቋም አካባቢ፣ በሰው ካፒታል እና ምርምር፣ መሠረተ ልማት፣ በገበያ ውስብስብነት፣ በንግድ ሥራ ውስብስብነት፣ በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ በፈጠራ ውጤቶች ላይ መሰረት በማድረግ እንደ ሀገር የተሰሩ ስራዎች የዳታ ክምችት ላይ መሰረት አድርጎ የሚሰጥ ደረጃ ነው፡፡

የግሎባል ኢኖቬሽን ኢንዴክስ ደረጃን ለማሳደግና መረጃን ለማጎልበት ከሚመለከታቸው ክልላዊና አለም አቀፍ ድርጅቶች አላማ እና ስልቶች መሰረት በማድረግ መሰብሰብ, ትንተና እና ሪፖርት ላይ በትብብርና በትኩረት መሰራት እንደለበት የመድረኩ ተሳታፊዎች አንስተዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ