+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ በአለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት / WIPO/ መደበኛ ጉባዔ ላይ በመሳተፍ ላይ ትገኛለች

በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልዱ ይመሰል የሚመራው የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን በአለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት / WIPO/ መደበኛ ጉባዔ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

ቡድኑ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከድርጅቱ ዳይሬክተር ጀነራል ዳረን ታንግ፣ ከWIPO የአፍሪካ ዲቪዥን ዳይሬክተር እና ከቅጂ መብት ልማት ከፍተኛ አስተባባሪ ጋር ተወያይቷል።

ውይይታቸው በኢትዮጵያ እና የአለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት /WIPO/ መካከል በሚጠበቁ የትብብር መስኮች ላይ ያተኮረ ነው።

ልዑካን ቡድኑን የሚመሩት የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልዱ ይመሰል ኢትዮጵያ ለአእምሯዊ ንብረት ዘርፍ ትኩረት መሰጠቷን አውስተው በዘርፉ ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው ጉዳዮች ለአቶ ዳረን ታንግ ገለፃ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ ከ WIPO ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር በተለይም የWIPO የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን በመጠቀም አእምሯዊ ንብረት በአገር ልማት ውስጥ ያለውን ሚና እና ፋይዳ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላትም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የሀገሪቱን የአእምሯዊ ንብረት ስነ ምህዳር ለማጠናከር በምታደርገው ጥረት WIPO ድጋፉን አጠናክሮ ለመቀጠል ያለውን ቁርጠኝነት አቶ ዳረን ታንግ አረጋግጠዋል።

አቶ ወልዱ ከWIPO የአፍሪካ ዲቪዥን ዳይሬክተር ሎሬታ አሲኢዱ እና የቅጂ መብት ልማት ከፍተኛ አስተባባሪ ሸሪን ግሬስ ጋር የተወያዩ ሲሆን በመከናወን ላይ ስላሉ ፕሮጀክቶች እና ወደፊት ስለሚጠበቁ ተግባራቶች ተነጋግረዋል፡፡

በጄኔቫ እየተካሄደ በሚገኘው በዚሁ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን እና በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ ሚስዮን ከሀምሌ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ