+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ከአጋር አካላት ጋር በትብብር የሚሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ገለፁ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከምስራቅ አፍሪካ ቀንድ የ“Giz” ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሠረተ-ልማት ኃላፊ እና የ“GovStack Open Source Community” ፕሮግራም አማካሪ ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መክረዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ተግባራዊነት ለማረጋገጥ እና በመንግሰት የሚሰጡ ኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶችን በማጥናት መስፈርት (ስታንዳርድ) እንዲወጣላቸው ከአጋር አካላት ጋር በትብብር መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በተለይም በአሁኑ ወቅት ወደ ስራ ለመግባት በመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የሚገኘውን የዲጂታል መንግስት 2030 ስትራቴጂን ቀይሰን እየሠራን ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የጀመርናቸው ሥራዎች ለማሻሻል ከሚደግፉ የተለያዩ የፕሮጀክት ሀሳቦችን ከያዘ እንደ “GovStack Open source Community” ፕሮግራም አጋር አካላት ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት ስላለን በቅድሚያ ፍኖተ-ካርታ ሊኖረን ይገባል ብለዋል፡፡

ከ“Giz” ኢትዮጵያ የ“GovStack Open-source Community” የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አማካሪ Mr. Thomas Pia Seiffaton በበኩላቸው የ“GovStack Open-source Community” ፕሮግራሞች የሚያካትታቸውን ተግባራት በዝርዝር አብራርተዋል።

የፕሮጀክት ሀሳብ የ“GovStack Open source Community initiative ዋነኛ ትኩረቱ በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ accelerating the digital transformation of government services” ላይ መሆኑን እና ተጠቃሚ የሆኑ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ልምዶችን አስገንዝበዋል።

ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር አብሮ መስራት ያለባቸውን ስራዎች ዝርዝር እና በቀጣይም በሚቀርቡበት ሁኔታ ዙሪያ ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር ተመካክረው የጋራ ፍኖተ-ካርታ ለማዘጋጀት የጋራ መግባባት ተደርጓል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ