+251118132191
contact@mint.gov.et
ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን በዘርፉ እውቀት ላይ በትኩረት መሰራት አለበት የሚኒስትር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ልዑል ስዩም ።
የቴክኖሎጂ ባለሙያው አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፉ የስራ ኃላፊዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥተዋል።
ስልጠናው በዲጂታል ዘርል ላይ ያለው የሰው ሀይል አቅም ለማጎልበትና የተሻለ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ ያለመ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ልዑል ስዩም እንደ ሀገር የያዝናቸውን እቅዶች ለማሳካት ቀጣይነት ያለው የሰው ሀይል ግንባታ ላይ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
በየጊዜው እያደገና እየተወሳሰበ የመጣውን የዲጂታል አለም ለመምራትና ለመጠቀም ወቅቱን መሰረት ያደረገ የአውቀት ባለቤት መሆን የፍላጎት ብቻ ሳይሆን የግዴታም ጭምር እንደሆነ ገልፀዋል።
ስልጠናውን የሰጡት አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ አለም በዲጂታልና በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ያሉበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከጊዜው ጋር የሚሄዱ እውቀቶችን መጋራት እንደሚጠይቅ አስገንዝበዋል።
በስልጠናው ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የተጠሪ ተቋማት፣ የክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋማትና ሌሎች የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል።
የተሰጠው ስልጠና ብዙ አቅምና ግንዛቤ የሚፈጥር ስለሆነ በዘርፉ ላይ ለተሰማሩ አካላት ሁሉ ቢሰጥና ቀጣይነት ቢኖረው ስራዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ከፍተኛ እገዛ እንዳለው ሰልጣኞች አንስተዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች