+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ በዲጂታል ዓለሙ ውስጥ ዋና ተዋናይ ለመሆን የሚያስችላትን አቅም ለመፍጠር የሰው ሀይል ግንባታ ላይ እየሰራች መሆኑ ተገለፀ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለሚኒስትር መስሪያ ቤቱ፣ ለተጠሪና ለክልል ተቋማት የስራ ሀላፊዎች የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

የዘርፉን ባለሙያዎች በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዙሪያ አቅም ለመገንባት ያለመውን ስልጠና የሰጡት የቴክኖሎጂ ባለሙያው አቶ ሰሎሞን ሙሉጌታ ናቸው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ በዲጂታል ኢኮኖሚ መሰረተ ልማትና በሰው ሀይል አቅም ግንባታ ላይ በትኩረት መሰራቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ያፋጥናል ብለዋል።

በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ስኬት ላይ የሚደረገው ፈጣን የትግበራ ስራዎች በሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተሰማ ገዳ ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማጎልበት የምታደርገውን ተግባር ተኮር ስራዎች በቅንጅታዊ አሰራር ስርዓት ለመምራት የሚያስችላትን አቅም በመፍጠር ዲጂታል ኢትዮጵያን 2025 እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

እየተሰጠ ያለው ስልጠና የዲጂታል አለሙ በአለማችን ኢኮኖሚ እድገት ላይ ያለው ሚና በመገንዘብ ሁሉም የነቃ ተሳትፎ እንዲኖረው እንደሚያደርግ ሰልጣኞች ተናግረዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ