+251118132191
contact@mint.gov.et
ኢትዮጵያ በጣሊያን እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው አለም አቀፍ የጠፈር ተመራማሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው።
ኮንፈረንሱ ''ኃላፊነት የተሞላበት የህዋ አጠቃቀም ለዘላቂነት'' በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ሲሆን ከ 11 ሺህ በላይ የዘርፉ ምሁራን፣ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም መሪዎች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።
በፕሮግራሙ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ፒ ኤች ዲ) እየተሳተፉ ሲሆን መድረኩ ለኢትዮጵያ የህዋ ፕሮግራም አለም አቀፍ አጋሮችን ለማግኘት የሚጠቅም መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።
ሚንስትር ዴኤታው በፈረንጆቹ በ2028 ጨረቃ ላይ ለሚደረግ የሰው አልባ መንኮራኩር ተልዕኮ ኢትዮጵያ አንዷ አካል እንድትሆን የሚያስችለውን ፕሮጀክት እየመሩ ሲሆን መድረኩ ኢትዮጵያ በዘርፉ ቀዳሚና ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር እንጠቀምበታለን ብለዋል።
አለም አቀፉ የህዋ ምርምር ፌደሬሽን ያዘጋጀው ይህ መድረክ በትምህርት ዘርፍም ሆነ ኢንደስትሪ ደረጃ በህዋ ላይ ያሉ አዳዲስ ክስተቶችንና የዘርፉ እድገት ያለበት ደረጃ ሁሉም ሰው እንዲያውቅ ለማደረግ የሚዘጋጅ ነው።
በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች በአንድ መድረክ እንዲገናኙና በጋራ መስራት የሚችሉባቸውን አማራጮች እንዲያዩም ለማስቻል ነው።
ፕሮግራሙን የጣሊያኑ ፕሬዝዳንት ሰርጊዮ ማቴሬላ የከፈቱት ሲሆን የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም፣ ከአውሮፓ የህዋ ኤጀንሲን ጨምሮ ከመላው አለም የተውጣጡ የጠፈር ተመራማሪዎች እየሳተፉ ነው።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች