+251118132191
contact@mint.gov.et
ኢትዮጵያ እና ህንድ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ስትራቴጂክ አጋርነትን ለማጠናከር በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር እና የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ ጋር በቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር፣ በፈጠራ ስራ ማጠናከር እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ያላቸውን ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማጠናከር በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ፈጣን እድገት ለማስመዝግብ ባደረገችው ጥረት ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሏንና በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚየስችላት እድል ለመፍጠር እየተጋች መሆኗን አንስተዋል፡፡
በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆነ የዲጂታል ስነምህዳር መገንባት ዓላማችን ነው ያሉት ሚኒስትሩ በሀገራችን የዲጂታል ቴክኖሎጂውን ዘርፍ ለማሳደግ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብርና በአጋርነት የሚሰሩ ስራዎች ትኩረታችን ናቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የዲጂታል ለውጥ ስራዋን በፍጥነት ለማሳደግ ስፔስ ሳይንስ፣ ጂኦስፓሻል መረጃ፣ ዳታ ማዕከላት እና ቴክኖሎጂ ማሸጋገሪያ እና ሌሎች አጋዥ ዘርፎች ላይ ከህንድ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል ቀድሞ የነበሩ የተላያዩ አጫጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን ለኢትዮጵያውያን የዩኒቨርስቲ መምህራን፣ ተመራማሪዎች እና ሲቪል ሰርቫንት ወጣቶች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር እና በአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ የሆኑት ክቡር አኒል ኩማር ራይ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ለይፋዊ ጉብኝት እንደሚመጡ ጠቅሰው በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
አምባሳደሩ ኢትዮጵያ በቅርቡ የጀመረችውን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እውቅና በመስጠት ለዚህ ህንድ በመተግበር ረገድ አጋር ለመሆን ያላትን ዝግጁነት በማጉላት ህንድን በትልልቅ ዲጂታል የህዝብ መሠረተ ልማት ላይ ያላትን ሰፊ ልምድ እንደምታጋራ ተጠቁሟል፡፡
የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ለመፍጠር በሚያስችል ጉልህ እርምጃ ስታርታፖች፣ ተመራማሪዎችን እና ፖሊሲ አውጪዎችን አንድ ላይ የሚያገናኝ ዓመታዊ የህንድ-ኢትዮጵያ የጋራ የፈጠራ ሳምንት እንዲቋቋም ሀሳብ አቅርበዋል።
በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የመግባቢያ ሰነድ ለማደስ እንደሚደረግና በሁለቱም ወገኖች በተመደቡ ባለሙያዎች ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገልጿል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች