+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ እየተገበረች ባለው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የተገኙ ውጤቶችን በማስፋት ለአህጉራዊና ቀጠናዊ ትስስር ልንጠቀምባቸው እንደሚገባ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ገለፀ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ከሰብ ሰሃራን አፍሪካ የቪዛ ገቨርናንስ ሶሉሺን ኃላፊ እንዲሁም ከቪዛ ዳይሬክተር ጋር የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማጎልበት በሚያስችሉ ዘርፎች መስኮች መክረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ኢትዮጵያ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት፣ በኤሊክትሮኒክ መንግስት፣ በኤሌክትሮኒክ ንግድ፣ ዲጂታል ክፍያ፣ ዲጂታል ታክስ አስተዳደር፣ ኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ፣ ኤሌክትሮኒክ ፊርማና የዚሁ ማሳለጫ በሆነው የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ያመጣችውን ለውጥና የወደፊት እቅድ ገለፃ አድርገዋል፡፡

አክለውም ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፉ ባደረገችው ሪፎርም የኢትዮጵያን ዲጂታላይዜሽን የሚያሳካ እመርታዊ ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን አውስተው እንደ ቪዛ ዓይነት ኩባንያዎች ጋር ተቀራርቦ መስራቱ ሚናው የላቀ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቪዛ ካርድ ዳይሬክተር አቶ ያሬድ እንዳለ በበኩላቸው እንደገለጹት በኢትዮጵያ ከፋይናንስ ዘርፉ ጋር በተፈጠረው መቀራረብ ከአስር ሚሊዮን በላይ የቪዛ ካርድ ተጠቃሚ መኖሩን አውስተው ይህን አሃዝ በመጨመር ወደ ላቀ ተጠቃሚ በማስፋት ለመስራት እቅድ አለን ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተተገበረው ሪፎርም ያመጣውን አዎንታዊ ለውጥ እንረዳለን ያሉት የሰብ ሰሃራ የቪዛ ሶሉሽን ኃላፊ ሚስ ፊሊስ ካማኡን የኢትዮጵያ መንግስት በዲጂታላይዜሽን ያሳየውን ቁርጠኝነት ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት በማስፋት የቀጠናዊ የዲጂታል ትስስር ለመፍጠርና የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማስፋት እድሉን እንጠቀምበታለን ብለዋል፡፡

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑ ባለቤት ከሆነው ተቋም ጋር በቀዳሚነትና ከሚመለከታቸው የፋይናንስና የንግድ ስራ የመንግስትና የግል ተቋማት ጋር መወያየታቸውን ያወሱት ሚስ ፊሊስ በተለያዩ ቦታዎች የሚታዩትን ያልተቀናጁ የዲጂታል ጅማሪዎችን በማስፋት ወደ ቀጣናዊና አህጉራዊ ደረጃ ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡

በምክክሩም ላይ በቀጣይ የባለሙያዎች ቡድን አቋቁመው የትብብር መስኮችን ለይተው ለመስራትና አገራዊ ወርክሾፕ በማዘጋጀት ከሁሉም ባለድርሻና አጋር አካላትን በማሳተፍ ወደ ትግበራ ለመግባት እንደሚሰራ ተጠቁሟል፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ