+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ እ.አ.አ ከ2000 አስከ 2022 ከ828 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለምርምር ግራንት ወደ ሃገር ማስገባቷ ተጠቆመ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ኢትዮጵያን ወክሎ የካውንስል አባል የሆነበት አለም አቀፍ የሳይንስ ግራንት ካውንስል (Science Grant Council Initiative) አና ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ሀገራት የግሎባል ምርምር ካውንስል (Sub-Sahara Regional Global Research Council) አመታዊ ጉባኤ በቦትስዋና ተካሂዷል።

በጉባኤው ኢኖስዒቲቭ ባስጠናው ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ እንደ አውሮፖውያን አቆጣጠር ከ2000 አስከ 2022 ከ828 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከተላያዩ አለም አቀፍ የምርምር ፈንድ አቅራቢዎች ማስገባትቷ ተገልጿል።

በዚህም ኢትዮጵያ ከ17 ሀገራት ውስጥ 6ተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን ኬንያ ቀዳሚ ስፍራን ይዛለች፡፡ጥናቱ በርካታ ጉዳዮችን ያካተተና በቀጣይ ለአባል ሃገራት በተጋጀው የዲጅታል ፕላትፎርም አማካኝነት ተደራሽ የሚደረግ ነው፡፡

ለ5 ቀናት በተካሄደው ጉባኤ በርካታ የጥናትና ምርምር ስራዎች የቀረቡ ሲሆን የአፍሪካን ኢኖቬሽን ከማጎልበት አኳያ ኢኖቬሽን ኤጀንሲዎች ሚና እና ኔትዎክ መመስረት፤ በምርምር ስራ የተለያዩ ሃገራት ተሞከሮ፤ የክትትልና ግምገማ ማዕቀፍ፤አንዲሁም በካወንስሉ አባል የአፍሪካ ሀገራት በትብብር የተሰሩ ምርመሮች ዙርያ ለአባል ሀጋራት ካውስንስል ተወካዮች ቴክኒካል ድጋፍ ከሚያደርጉላቸው አካላት ጋር ውይይቶች ተደርገዋል፡፡

በጉባኤው በተካሄዱ የፓናል ውይይቶች ላይ እና ሌሎች ፕሮግራሞች ላይ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የምርምር ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ እንዲሁም የኢኖቬሽን ልማት መሪ ስራ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ በኢትዮጵያ በኩል ያለውን ተሞክሮና የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን አቅርበዋል።

የሳይንሰ ግራንት ካውንስል ኢኒሼቲቭ 17 የአፍሪካ ሃገራትን ምርምርና ኢኖቬሽን እንቅስቃሴዎችን የሚደግፉ አካላትን አቅም ማጠናከር አላማ አድርጎ በIDRC(ካናዳ) ፣ FCDO (UK), NRF( ደቡብ አፍሪካ), Sida (ስዊድን), DFG (ጀርመን) አና ኖርዌ መስራችነት ሌሎች የቴክኒካል ኢጀንሲዎችና አጋሮችን በማካተተ በ2015 የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ ነው፡፡

ኢኒሼቲቩ በምዕራፍ 1 እና 2 ተከፍሎ ከ2015 እስከ 2025 አየተገበረ ሲሆን ሶስተኛው ምዕራፍ ከ2026 ጀምሮ ለመተግበር በዝግጅት ላይ ነው፡፡

በዋናነት ትኩረት የሚያደርገው፤ የአባል ሃገራት የምርምርና ኢኖቬሽን ግራንት የመስጠት አቅም፤ በምርምርና ኢኖቬሽን የግል ዘርፍ ተሳትፎ ፤ የምርምር አስተዳደር አቅም፤ የትብብር ፕሮጀክቶች፤ ስትራቴጂክ ግንኙነትና የምርምር ውጤቶችን የመጠቀም አቅም፤ አካታችነት አና አዳዲስ የኢኖቬሽን ፈንዲንግ ኤጀንሲዎችን የማቋቋም አቅም መገንባት ላይ ነው፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ