+251118132191
contact@mint.gov.et
ኢትዮጵያ ከማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ዘርፍ የምታገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂን መጠቀም እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ይሹሩን አለማየሁ (ፒ ኤች ዲ) ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ሜካኒካል ኢንጅነሮች ማህበር “የማኑፋክቸሪንግ ቅልጥፍናን እና ዘላቂነትን በስማርት ቴክኖሎጂ እና ሰውን ማዕከል ባደረገ ዲዛይን ማሳደግ” በሚል መሪ ቃል 27ኛው አመታዊ የፓናል ውይይት አካሂዷል።
በስብሰባው ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ የሀገራችንን ኢኮኖሚ እድገት ለማጎልበት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ላይ የስራ እድል ከመፍጠርም አልፎ ሁሉም ተዋናዮች በንቃት እንዲሳተፉበት የሚያስችል ስነምህዳር ለመገንባት መንግስት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ቁልፍ ከሚባሉ ዘርፎች አንዱ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ሲሆን በተለይ አለም በአሁኑ ወቅት ወደ Industry 5.0 እየገባ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው የዲጂታል ቴክኖሎጂን መጠቀም የግድ ይላል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የዓለም ኢኮኖሚ እድገት የደረሰበት ምዕራፍ ላይ ለመድረስ መንግስት ብቻውን ሳይሆን ሁሉም በትብብር የዘመነውን የቴክኖሎጂና የዲጂታል ዘርፉን ክህሎት በማጎልበትና በመጠቀም ብቁና ንቁ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ ሜካኒካል ኢንጅነሮች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙዓዝ በድሩ የማኑፋክቸሪንግ ምርታማነት እና ዘላቂነትን ለማሳደግ እንደ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ (IoT)፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና የተደራጀ የመረጃ ትንተናን በሰው ተኮር መርህ የምህንድስና ንድፈ ሀሳቦችንና የዲዛይን መርሆችን በማዋሃድ የተሳለጡ የምርት ሂደቶችን መፍጠር ይገባል ብለዋል።
አክለውም በምርት ሂደት ላይ ብክነትን በመቀነስ ፣ የተሻለ የስራ ከባቢ እንዲኖር በማስቻል ዘላቂና ውጤታማ አምራች ኢንዱስትሪን ለመፍጠር ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
በመድረኩ የማህበሩ አጠቃላይ እንቅስቃሴና በተመረጡ ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ የመከረ ሲሆን የትብብር ስራዎችን ለማጠናከር የግንኙነት ጊዜውን ማብዛት እንደሚገባ ተገልጿል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች