+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ ከ29 ሀገራት ጋር በመሆን የዓለም አቀፍ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትብብር ድርጅትን መሰረተች

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ፤ ሐሙስ ዕለት በሻንጋይ በተካሄደው የዓለም አቀፍ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትብብር ድርጅት (WAICO) ማቋቋሚያ ስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት ስምምነቱን በኢትዮጵያ ስም ፈርመዋል።

የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ የተከናወነው በተመሳሳይ በሻንጋይ እየተካሄደ ባለው የ2026 የዓለም አቀፍ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ (WAIC) ዋዜማ ላይ ነው።

በአጠቃላይ 29 ሀገራት ስምምነቱን በመፈረም የዚህ አዲስ ነፃ መንግስታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት መስራች አባላት ሆነዋል።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በቻይና መንግስት ስም የፈረሙ ሲሆን፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከተገኙት ተወካዮች መካከል አንዱ ነበሩ።

በስምምነቱ መሠረት የድርጅቱ (WAICO) ዋና መሥሪያ ቤት በሻንጋይ ይሆናል። ድርጅቱ የተመድ ቻርተር ዓላማዎችን የሚያከብር፣ ለሰፊ ምክክርና ለጋራ ጥቅም በጋራ ለማበርከት ቁርጠኛ የሆነ እንዲሁም ሰውን ማዕከል ያደረገ አካሄድን የሚከተል ይሆናል።

ዓላማውም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ ዓለም አቀፍ ትብብርን እና ዓለም አቀፍ አስተዳደርን ማሳደግ ሲሆን፤ ይህም የኤአይ (AI) ልማት ለመላው የሰው ልጅ ጠቃሚ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ በሆነ አቅጣጫ እንዲጓዝ ለማድረግ ነው።

የኢትዮጵያ ተሳትፎ ሀገሪቱ ለአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ለዲጂታል ሽግግር እያሳየች ያለውን እያደገ የመጣ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በስኬት የተጠናቀቀውን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴን፣የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና የብሔራዊ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መቋቋምን ጨምሮ የተለያዩ ተነሳሽነቶችን በንቃት ሲያስተባብር ቆይቷል በማስተባበር ላይም ይገኛ።

ከዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ በመረጃ ሀብቶች፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና በዲጂታል ልማት ላይ ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት መጥቀሳቸው የሚታወስ ነው።

የዓለም አቀፍ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ድርጅትን (WAICO) የማቋቋም ሃሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና የቀረበው በሐምሌ ወር 2025 (እ.ኤ.አ) ሲሆን፤ ዓላማውም የኤአይ (AI) ልዩነትን ለማጥበብ እና ከቴክኖሎጂው የሚገኘው ትርፍ ደቡባዊው የዓለም ክፍል (Global South) ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል ዘርፈ-ብዙ መድረክ ለመፍጠር ነው።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ