+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ የስታርታፕ ስነ-ምህዳርን በማጎልበት ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን በትብብርና በትኩረት እየሰራች ነው ዶ/ር ባይሳ በዳዳ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ አልጀረስ ከተማ የኢትዮጵያ ስታርታፖች የተሳተፉበትን 3ኛው የአፍሪካ ስታርታፕ ዓውደ ርዕይን የአልጄሪያ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጎበኙ፡፡

የአፍሪካ ስታርታፕ ዓውደ ርዕይ የፈጠራ ባለሙያዎችን በማብዛትና ስታርታፖችን ወደ ግዙፍ ካንፓኒዎች በማሳደግ ከዘርፉን የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ ያለመ ነው፡፡

በዓውደ ርይዩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ አፍርካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ የሚያስችላትን የስታርታፕ ስነምህዳር ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን 3ኛው የአፍሪካ ስታርታፕ ዓውደ ርዕይ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የፈጠራ ስራዎች አድገው ስታርታፕ በመሆን ከፍተኛ የስራ እድል ከመፍጠር አልፎ ዜጎች የሀብት ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻሉን ገልፀዋል፡፡

በጉብኝቱ የተስተዋሉት የስታርታፕ ስራዎች አፍሪካ ያላትን እምቅ አቅም ለኢኮኖሚ እድገቷ ዋነኛ ሞተር አድርጋ መጠቀም እንደሚያስችላት ተናግረዋል፡፡

በአልጀሪ የኢትዮጵያ አምባሳዶር ሙክታር መሃመድ፣ የአልጀሪያ Minister of Knowledge Economy, Startups, and Micro-enterprises ሚኒስትር፣ ከ45 የአፍሪካ ሀገራት የተገኙ ሚኒስትሮች እና ኢንቨስተሮች፣ በአውደ ርይዩን ጉብኝት ላይ ተገኝተዋል።

በአልጀርስ ከተማ እየተካሄደው ያለው የአፍሪካ ስታርታፕ ጉባኤ እና ዓውደ ርዕይ ብዙ ልምድ የሚገኝበትና ለስታርታፕ ስነ-ምህዳር ግባታ ከፍተኛ ሚና እዳለው እና ከኢንቨስተሮች ጋር ለመስራት እድል እንደሚፈጥር ተጠቁሟል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ