+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢትዮጵያ የዲጂታል ጉዞዋን እውን የሚያደርጉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ረገድ ስኬታማ ስራዎችን መስራቷን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ፒ ኤች ዲ) ተናገሩ።

''ኢንተርኔት ላይ የተመሰረተ ስራ ፈጠራ ለአፍሪካ የዲጂታል እድገት'' በሚል መሪ ቃል አሊባባ ከኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማህበር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 'የአሊባባ ግሎባል ተነሳሽነት መሰባሰቢያ መድረክ' በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

መድረኩ አህጉራትን በማገናኘት የአሊባባ እና

የወደፊት የአፍሪካ ዲጂታል ኢኮኖሚ ሥራ ፈጣሪነት ማጎልበት፣ ዲጂታላይዜሽን በማሳደግ

ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት በኢትዮጵያ፣ ለመገንባትና የአፍሪካ ሴቶችን በማበረታታት ሥራ ፈጣሪዎች ለማድረግ ያለመ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ፒ ኤች ዲ) ኢትዮጵያ የዲጂታል ጉዞዋን እውን የሚያደርጉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ረገድ ስኬታማ ስራዎችን መስራቷን ተናግረዋል።

ዘላቂና አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ መገንባት ቅድሚያ የምንሰጠው ስራችን ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በአይ ሲ ቲ መሰረተ ልማት፣ በዲጂታል ክህሎት እና በህግ ማዕቀፍ ዝግጅት ረገድ የተሳካ ስራ ሰርተናል ብለዋል።

የዲጂታል ዘመኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መቀበል ብቻ ሳይሆን የፈጠራ አስተሳሰብን ማሳደግ እንደሚፈልግ ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታው ወጣቶች የዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮች ሚኒስትር አማካሪ ሚስተር ያንግ ይሀንግ በአለም አቀፍ የዲጂታል ተሰጥኦ ስልጠና፣ በስራ ፈጠራና በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ትብብርን ማጎልበት ላይ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ አንስተዋል።

ኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎችን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሳደግ በዲጂታሉ አለም የንግድ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችሉ ስነ-ምህዳርን በጋራ እንገነባለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ሽርክና በመፍጠር ረገድ እንደ አሊባባ ካሉ ተቋማት ጋር በትብብር በተለያዩ ዘርፎች ላይ ስራዎችን እየሰራች እንደሆነ ከተሳታፊዎች ተነስቷል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ