+251118132191
contact@mint.gov.et
ኢንዱስትሪዎች በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ በመታገዝ መስራት አለባቸው
ኢንዱስትሪዎች በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ታግዘው ጥራቱን የጠበቀ ምርት ማምረት እንዳለባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሦስተኛውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በይፋ መርቀው መክፈታቸው ይታወሳል።
በዚህም የኤክስፖው አካል የሆኑ ፓናል ውይይቶች በተለያዩ ባለድርሻ አካላት በመካሄድ ላይ የሚገኙ ሲሆን በመድረኩ በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ላይ ያተኮረ ውይይ ተካሂዷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ኢንዱስትሪዎች በምርትና አገልግሎት አሰጣጥ ተወዳዳሪ ለመሆን ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ሊታገዙ ይገባል፡፡
ከለውጡ በኋላ የተጀመረው የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂና የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ፕሮግራም የዜጎችን የቴክኖሎጂ ክህሎት ከማዳበር ባለፈ ለግሉ ዘርፍ ምቹ አውድ የፈጠረ ነው ብለዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ዘመኑ የደረሰበት የ4ጂ እና 5ጂ ኔትወርክ ተደራሽ በማድረግና የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝ በማድረግ ረገድም ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም ግልጽነትና አስተማማኝነት ያለው አገልግሎት የሚሰጡ ኦንላይን ፕላትፎርሞች መፈጠራቸው በዘርፉ ለተገኙ ለውጦች ማሳያ መሆናቸውን አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት የውጭ ምንዛሪ ወጪን ለመቀነስ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
የፈጠራ ውጤቶች ለማስፋትና የፈጠራ ሃሳቦችን በማዳበር ወደ ተግባር ለመቀየር በኢኖቬሽን ማዕከላት እና በዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ሊንኬጅ አማካኝነት የጥናትና ምርምር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች በፈጠራ ውጤታቸውና በቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸው ለአነስተኛና መለስተኛ ኢንዱስትሪዎች ምርጥ ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ በጥናትና ምርምር የመደገፍ ስራ በመሰራት ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል ፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች