+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዲስ አበባ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስትቲዩት (ILRI)

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዲስ አበባ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስትቲዩት (ILRI) ካምፓስ ውስጥ ከምርምር ማዕከላት ጋር የግብርና ምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ለመደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በመምከር የጉብኝት መርሃ ግብር አካሂዷል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የተመራው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮችን ያካተተው ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስትቲዩትና የሲጂአይአር የምርምር ፕሮግራሞችን ስራዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የሀገራችንን የግብርና ዘርፍ በማዘመን የምንሻውን ውጤት ለማምጣትና ኢኮኖሚውን ለማጎልበት ጊዜውን የዋጀ የቴክኖሎጂ አስተዋፅዖ ልንጠቀምበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ሀገራችን ለግብርናው ዘርፍ የሰጠችውን ትኩረት በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሊታገዝ ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ የግብርና ምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን ስኬታማነት ለማረጋገጥ በትብብር ላይ የተመሰረቱ ስራዎች ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት እንደሚሹ ገልፀዋል።

አለም በቴክኖሎጂ ጥብብና ጉልበት ላይ እበለፀገች ነው ያሉት ሚኒስትሩ የምርምር ዘርፉ የሚፈታውን ውስብስብ ተግዳሮት በአጭር ጊዜ መፍትሔ ለመስጠት የቴክኖሎጂው እውቀት ወሳኝ ሚና እንዳለውና መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል።

የ ILRI Director General’s Representative to Ethiopia Dr. Namukolo Covic ዘርፉ ለተደጋጋሚ እና ለተስፋፋው ድርቅ እና ሌሎች ከአየር ንብረት ጋር በተያያዙ የተፈጥሮ አደጋዎች እየተጋለጠ ስለሆነ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሊታገዝ እንደሚገባ አንስተዋል።

የግብርና ምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን ለማሳካት የቴክኖሎጂውን ሚና ለመጠቀም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመሰራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

የሰብል ቴክኖሎጂ እና ማሻሻያ፣ የሰብል አያያዝ፣ ድህረ ምርት እና አጠቃቀም፣ የዘር ስርዓት ቴክኖሎጂዎች እና የብሔራዊ ግብርና ምርምር ስርዓቶችና አቅም ግንባታ ላይ በጋራ ለመስራት ቀጣይነት ያለው የግንኙነት አቅጣጫም ተቀምጧል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ