+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በሳይንሰ፣  ቴከኖሎጂና ኢኖቬሸን ዘርፍ በክህሎት የዳበረ ብቁ አመራርን ለመፍጠር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በሳይንሰ፣ ቴከኖሎጂና ኢኖቬሸን ዘርፍ በክህሎት የዳበረ ብቁ አመራርን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመፍጠር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነቱን ሰነድ ፈርመዋል፡፡
የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሀገሪቱ በሳይንሰ፣ቴከኖሎጂና ኢኖቬሸን ባህል እንዲዳብርና የሰው ሀብት አመራሩን በማብቃት ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ በማሸጋገር ኢትዮጵያ የጀመረቻቸውን ለውጦች በማፋጠን ላይ የተመሰረተ ስራ ከሰራን በአጭር ጊዜ ግባችንን እናሳካለን ብለዋል፡፡
በዘርፉ ብቁ መሪ መፍጠር ለኢትዮጵያ ወሳኝ ሚና አለው ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ሀገራችን የዲጅታል ኢኮኖሚውን ለማበልፀግ በኢኖቬሽን ዘርፉ ላይ አቅም ያለው የሰው ሀይል ለመፍጠር የሚያስችል ስርዓት በመገንባት ላይ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ሀገራት በአንድ ዘርፍ ብቻ ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ የሚያደርጉት ጥረት ብዙም ውጤት ሲያመጣ አይስተዋልም በመሆኑም እኛም ግብርና ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚያችንን አድማሱን ለማስፋት እንደ ሀገር ብዙ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በኢኖቬሽን ብቁ የሆነ ለህዘብ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችሉ በስራቸውና በምግባራቸው ብቁ አመራሮችን በየደረጃው በብዛት በመገንባት የኢትዮጵያ ብሎም የአፈሪካን ሁለንተናዊ ብልጽግና በዘላቂነት ለማሳካት ወሳኝ ሚና እንዳለው አንስተዋል፡፡
ከአለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚነሱ ሀሳቦች ላይ ጥናት እና ምርምር በማካሄድ ስልጠናዎችን በመስጠት ለተሳካ ሀገራዊና ተቋማዊ ግንባታ እውን መሆን ኃላፊነቱን መወጣት የሚችል አመራር ማፍራት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 
ሀገራዊ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ከመቸውም ጊዜ በመፍጠን ያለውን አቅም አሟጦ በመጠቀም ከመፈራረም ባለፈ አጋርነቱን በማጠናከር ወደ ስራ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ