+251118132191
contact@mint.gov.et
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የተመራ ልዑካን ቡድን በባህር ዳር ከተማ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስራዎችን ተዟዙሮ ጎበኘ
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በዶ/ር በለጠ ሞላ የተመራ ልዑካን ቡድን በባህር ዳር ከተማ የተለያዩ ተቋማት ስራዎቻቸውን ዲጂታላይዝ በማድረግና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተሻለ አቅም ለመፍጠር እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ጎብኝተዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ
ሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ላይ ፈጣን ለውጥ ለማምጣትና ከብልሹ አሰራር ስርዓት ለመውጣት ስራዎችን ዲጂታል ከማድረግ ውጪ አማራጭ እንደሌለ ገልፀዋል።
ዲጂታልን ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት መጠቀም ግዴታ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የሀገራችንን የኢኮኖሚ እድገት ለማጎልበት የአሰራር ስርዓቱ የሚሻውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት ላይ ሁሉም በየዘርፉ በትኩረት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በባህር ዳር ከተማ ተቋማት በዲጂታል ዘምነዋል ያሉት ሚኒስትሩ በከተማ በተለያዩ ተቋምት ላይ የተሰሩ ውጤታማ የዲጂታል ስራዎች የማህበረሰቡን ፍትሃዊ አገልግሎት ለመፍጠር፣ ጊዜንና ሀብትን ለመቆጠብ የሚያስችሉ ስርዓቶች በመፈጠሩና ውጤት በመምጣቱ አድናቆትን ቸረዋል ።
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ ኢትዮጵያ የዲጂታል ጉዞዋን እውን የሚያደርጉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራች መሆኗን አስገንዝበዋል።
ዘላቂና አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ መገንባት ቅድሚያ የምንሰጠው ስራችን ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ተቋማትን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተሰራው ሰራ የሚጠበቀውን ውጤት ማምጣት መቻሉን ማየት መቻላቸውን ገልፀዋል።
በባህር ዳር ከተማ በዲጂታል ኢኮኖሚው ላይ እየተሰሩ ያሉ አመርቂ ስራዎች ቢሆኑም ከዚህ በላይ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በጉብኝት ቡድኑ ተጠቁሟል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች