+251111265737
contact@mint.gov.et
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ክብርት ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በአፍሪካ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ የፈጠሩ 100 ሴቶች ዝርዝር ውስጥ በመካተታቸው የተሰማውን ልባዊ ደስታ ይገልጻል።
ይህ እውቅና በአፍሪካ ሃይፐርስኬለርስ እና ዘ-ሊትልስቴፕስ ግሩፕ በተሰኙ አህጉር አቀፍ ተቋማት የተበረከተ ሲሆን፤ ክብርት ሚኒስትሯ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ በነበሩበት ወቅት የዲጂታል መሰረተ ልማት በማስፋፋት፣ በዲጂታል ፋይናንሲንግ እና የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እውን በማድረግ ረገድ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ነው።
ይህ ሀገራዊ ስኬት ለእነዚህ አበይት ውጤቶች መመዝገብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ የመላው ሰራተኞች፣ አጋሮች እና ባለድርሻ አካላት የጋራ ጥረት ማሳያም ጭምር ነው።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራር እና መላው ሰራተኞች ለዚህ ታላቅ ስኬት የተሰማንን ደስታ እየገለጽን፤ ለክብርት ሚኒስትሯ አካታች፣ ፈጠራ የታከለበት እና በዲጂታል የበለጸገች ኢትዮጵያን የመገንባት ሀገራዊ ተልዕኮን በማሳካት ረገድ ቀጣይነት ያለው ስኬት እንዲቀናጁ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን።
ለተጨማሪ፡-
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251111265737
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች