+251118132191
contact@mint.gov.et
እንደ ሀገር ጠንካራ የቴክኖሎጂ ተቋማት ለመገንባት ወቅቱን የሚዋጅ የእውቀት ባለቤት የሆነ አመራር መገንባት እንደሚገባ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ገለፁ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ለተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች የዲጂታልና የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ እውቀት ለማስታጠቅ የሚያስችል የስልጠና መድረክ አካሄደ።
ስልጠናው በየጊዜው በፍጥነት እያደገ የሚሄደውን የዲጂታልና የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም መምራት የሚችል የመንግስት አመራር ለመፍጠር ያለመ ነው።
በስልጠናው ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ በዓለም ተወዳዳሪ የሆነ የቴክኖሎጂ ተቋም ለመገንባት ለዘርፉ አመራር የማይቋረጥና ተከታታይ የሆነ አቅም ግንባታ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
አሁን ያለው የቴክኖሎጂ እድገት የዘርፉ ተዋናዮች ከጊዜው ጋር የሚሄድ እውቀት ተላብሰው እንዲገኙ ያስገድዳል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የተቋማቱ አመራሮች የተፈጠረላቸውን ቀጣይነት ያለውን የስልጠና እድል በሙሉ አቅም በመጠቀም በፍጥነት ተለዋዋጨ ለሆነው ለመፃኢ የቴክኖሎጂ ዕድገት ግዳጅ ራሳቸውን እንዲያበቁ አሳስበዋል።
የቴክኖሎጂ እውቀት ሁሌም አትራፊ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የቴክኖሎጂ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች እየተወሳሰበና እየረቀቀ የመጣውን የቴክኖሎጂ ስርዓት ለመምራት በዘርፉ ራስን ማብቃት ውዴታ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ስልጠናው ከአመራርነት ባሻገር ዜጋን ያማከለ የአርፊሻል ኢንተለጀንስ (AI ) መፍትሄዎችን እንዲነድፉ፣ ተቋማዊ ቅልጥፍናን እንዲያሳድጉ እና ኃላፊነት የተሞላበት ፈጠራን የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችን እንዲቀረፁ የሚያግዝ መሆኑን ተጠቁሟል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች