+251118132191
contact@mint.gov.et
ከእንሰት እሴት የተጨመረባቸው ምግቦችን ማምረት የሚያስችል የምርምር እና የፈጠራ ስራ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት በተሞክሮነት ለእይታ ቀረበ።
በኢትዮጵያ የተሰራው የምርምር እና የፈጠራ ስራ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት በተሞክሮነት ቀርቧል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ በመተባበር የተሰራው የምርምር እና የፈጠራ ስራ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት በተሞክሮነት ቀርቧል።
ምርምርና ፈጠራ በዋናነት ከእንሰት እሴት የተጨመረባቸው ምግቦችን ማምረት የሚያስችል የምርምር እና የፈጠራ ስራ ውጤት ሲሆን፤ ምርቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ የገበያ ፍላጎት እየጨመረ የመጣውን የእንሰት ምግቦችን ለማሰተዋውቅ ያለመ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ምርምሩን ከመጀመሪያው አንስቶ አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግና ከየባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን ከውጪ ፈንድ በማምጣት ወደ ምርት እንዲገባ እና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር ወደ ማህበረሰቡ ለማድረስ በትብብር የተሰራ ሲሆን በቀጣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልል ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
በዶ/ር አዲሱ ፍቃዱ የሚመራው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቡድን እንሰትን ከባህላዊ አሰራር ወደ ዘመናዊ ምግብ በመቀየር የሚያስችሉ አዳዲስ የምርምር እና የፈጠራ ውጤቶችን በተሞክሮነት አቅርበዋል።
ምርምሩ ድርቅን በመቋቋም የኢትዮጵያ ገፀበረከት የሆነውን ከእንሰት የሚገኘውን ምግብ በምርምርና በቴክኖሎጂ በማዘመን ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ ሆኖ ገቢ የሚያስገኝበትን ስርዓት ለመፍጠር የተሄደበት ጉዞ ስኬታማነቱን በአለም ደረጃ ማረጋገጥ አስችሏል ።
በኢትዮጵያውያን የተሰራው የእንሰት ምርምር እና ፈጠራ ስራ ውጤት በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ (STI) 2025 ፎረም ላይ ግንቦት 9 ቀን 2025 በተሞክሮነት መቅረብ ችሏል።
በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ለምግብነት የሚጠቀሙትን የእንሰት ተክል በማዘመን ከሀገራችን ዋና የምግብነት ፍጆታ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እንደቡናችን ተፈላጊ እንዲሆን ዘርፈ ብዙ ስራዎች በመሰራታቸው ግቡን ሊያሳካ ችሏል።
በተጨማሪም፣ ይህ ፈጠራ የተባበሩት መንግስታት የ2030 የልማት ግብ ለማሳካት የሚከናወኑ ስራዎችን በሳይንስ እና በፈጠራ ስራ በማገዝ ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ፤ ፈጠራውም የተባበሩት መንግስታት ዘላቂ የልማት ግቦች (SDGs) ማለትም Zero Hunger (SDG 2)፣ Good health and wellbeing (SDG 3)፣ Gender Equality. (SDG 5)፣ Decent Work and Economic Growth (SDG 8)፣ Climate action (SDG 13) እና Partnership for the Goals (SDG 17) በቀጥታ ተደራሽ በማድረጉ ለሌሎች ሀገራት በተሞክሮነት እንዲቀርብ ተደርጓል
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች