+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ከ100 በላይ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን ወስደዋል።

የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን ለወሰዱ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፖሻል ኢንስትቲዩት ሰራተኞች እውቅና ተሰጥቷል።

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፣በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ እና ዳታ ሳይንስ ዘርፎች ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የተዘጋጀውን ነጻ የኦንላይን ሥልጠና በሀገር አቀፍ ደረጃ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

የተጠሪ ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴ በሚጎበኝበት መድረክ ላይ ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች እውቅና የሰጡት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ስልጠና በመውስድ ዲጂታል ክህሎትን ማዳበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ስልጠናውን ዩንቨርሲቲ ተማሪውች፣መምህራን፣የተቋማት ሰራተኞችና ሌሎች ወጣቶች በመውስድ ላይ ናቸው።

በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፖሻል ኢንስትቲዩት 100 በላይ ሰራተኞች ስልጠናው መውሰዳቸው በእውቅና አሰጣጥ መርህ ግብር ላይ ተገልጿል።

የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችለውን ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ በዚህ ሊንክ ላይ ይመዝገቡ።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ