+251118132191
contact@mint.gov.et
ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ሆነው ተሹመዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዲስ ሚኒስትር ድኤታ ሆነው ለተሾሙት ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በምክትል እና በዋና ዳይሬክተርነት ያገለገሉ ሲሆን ከሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተቋሙ የአይሲቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ሆነው ተሹመዋል።
በአቀባበሉ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የአይ ሲ ቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ከፍተኛ ሃገራዊ ትኩረት የተሰጠው ዘርፍ መሆኑን ጠቅሰው ለውጤታማነቱ ከተቋሙ አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በትጋት እንደሚሰሩ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአይ ሲ ቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች
©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ