+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ በተገኙበት የኢትዮ ክላውድ ታለንት ፕሮግራም ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ተጀመረ

በኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ እና ዘርጋዉ ክላውድ ትብብር የተዘጋጀው የኢትዮ ክላውድ ታለንት ፕሮግራም ዛሬ በማቅ ተጀምሯል።

በመክፈቻ ፕሮግራሙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና በመንግሥት ከዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አንፃር እየተወሰዱ ያሉ የፖሊስና ስትራቴጂዎችን ገልፀዋል።

በተለይም የክቡር ጠ/ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢንሼቲቭ ጀምሮ ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር የሚሰሩ ስራዎችን አብራርተዋል። ከሰው ሃብት ልማት አንፃር በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በኩል በቡራዩ ታለንት ልማት ትምህርት ቤት የታቀዱ ስራዎችን ጨምሮ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ በኩል በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን ለተሳታፊዎቹ ማብራሪያ ስጥተዋል።

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ አህመድም በበኩላቸው የኢትዮ ክላውድ ታለንት ፕሮግራም በተለይ ከከፍተኛ ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎች ከዳታ ሴንተር ፋሲሊቲ ጀምሮ እስከ ክላውድ አገልግሎት የተግባር ስልጠና ለመስጠት ታስቦ የተጀመረ መሆኑን አስረድተዋል። በመጀመሪያ ዙር 20 ሰለጣኞችን የተቀበሉ መሆኑን ገልፀው በ2017 ዓ.ም. እስከ 500 ተማሪዎችን ለማሰልጠን መታቀዱን ገልፀዋል።

 

 

 

 

 

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ