+251111265737
contact@mint.gov.et
ክብርት ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ ከባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮች ጋር በአምስት ዓመታት አፈጻጸም እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሄዱ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ ከሚኒስትር ድኤታዎችና ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር በመሆን፣ የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (BETIn) ባለፉት አምስት ዓመታት ያከናወናቸውን ስኬታማ የምርምር ሥራዎች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ተቋማዊ አቅሞችን በጋራ በመመልከት በቀጣይ ተግባራት ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ወቅት የተሻሻሉ የበቆሎና የሩዝ ዝርያዎች፣ የዘመናዊ እንሰት ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂ፣ የቦረና ከብቶች ጄኔቲክ ማሻሻያ፣ የዶሮ ክትባቶችና የኢንዱስትሪ ማሽኖች ተዘጋጅተው ለተጠቃሚዎች በመድረስ ለምግብ ዋስትናና ለጤና ዘርፍ ያበረከቱት አመርቂ አስተዋጽኦ ተመላክቷል።
በተጨማሪም ተቋሙ በርካታ በውጭ ፈንድ የሚደገፉ ዓለም አቀፍ የምርምር ፕሮጀክቶችን በስኬት እያስተዳደረ ይገኛል። ክብርት ሚኒስትሯ በተመዘገቡት አበረታች ስኬቶች የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታና አድናቆት ገልጸው፣ የተገኙት የምርምር ውጤቶች የዜጎችን ሕይወት በቀጥታ የሚቀይሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ይበልጥ ለላቀ ሀገራዊ ተጠቃሚነትም እነዚህን የምርምር ግኝቶች ወደ ተጨባጭ ገበያ በማሸጋገር (ኮሜርሻላይዝ በማድረግ)፣ ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከሥነ-ምኅዳሩ መንግሥታዊና የግል ባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም የዘርፉን ተወዳዳሪነት ይበልጥ ለማሳደግ፣ የሀብት ብክነትን ለመቀነስና ያሉ አቅሞችን በጋራ ለመጠቀም ለመላው ኢትዮጵያ አገልግሎት የሚሰጥ ብሔራዊ የጋራ ላብራቶሪ መገንባት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል።
በመጨረሻም ክብርት ሚኒስትሯና የልዑካን ቡድኑ የኢንስቲትዩቱን ዘመናዊ ላብራቶሪዎችና የሥራ ፋሲሊቲዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
#MInT#BETIn #BioTechnology #Innovation #DigitalEthiopia
Ethiopian Communications Authority
Ethiopian Intellectual Property Authority/EIPA የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251111265737
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች