+251111265737

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ክብርት ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ የብሔራዊ ክላውድ ዳታ ማዕከልን ዝግጁነት በመገምገም፤ የተበታተኑ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶችን በሚያስቀር መልኩ ሀገራዊ የፖሊሲ አቅጣጫ እንዲቀመጥ አቅጣጫ ሰጡ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ በግንባታ ላይ የሚገኘውን ብሔራዊ የክላውድ ዳታ ማዕከል አሁናዊ ቁመና በመጎብኘት የፕሮጀክቱን ዝግጁነት ገምግመዋል። ማዕከሉ ዓለም አቀፍ ስታንዳርዱን ጠብቆ እየተገነባ መሆኑን ያረጋገጡት ሚኒስትሯ፣ ቀሪ ሥራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ ሙሉ ኦፕሬሽን በማስገባት የሚጠበቀውን ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጥ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ይህ ግዙፍ መሠረተ ልማት መገንባቱ በየተቋማቱ የሚደረጉ የተበታተኑ አነስተኛ የዳታ ማዕከል ኢንቨስትመንቶችን በማስቀረት የሀብት ብክነትን የሚታደግ ቁልፍ ስትራቴጂያዊ እርምጃ መሆኑን ሚኒስትሯ አብራርተዋል። አካሄዱ ከመንግሥት «መደመር» እሳቤ ጋር በወሳኝነት የሚቆራኝ በመሆኑ፣ ተቋማት ውስን ሀብታቸውን አቀናጅተው በአንድ ማዕከላዊና ደህንነቱ በተጠበቀ ብሔራዊ መሠረተ ልማት ላይ እንዲመሠረቱ ተገልጿል።

ዳታ ማዕከሉ የ«ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» ራዕይን ለማሳካት የጀርባ አጥንት ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፣ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥ በተሻለ አቅም፣ ጥራትና ደህንነት ለማቅረብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሀገራዊ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥና የስነ-ምኅዳሩን ስታንዳርድ በመቆጣጠር የመንግሥትና ብሔራዊ አገልግሎቶች አስተማማኝና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ እንዲስተናገዱ ያደርጋል።

በተመሳሳይ ጉብኝት ክብርት ሚኒስትሯ በኢኖቢዝ-ኬ ኢትዮጵያ ማዕከል በመገኘት የስታርታፕ ድርጅቶችን ሥራዎች ተመልክተዋል። ማዕከሉ የፈጠራ ሐሳቦችን ወደ ተጨባጭ ምርትና አገልግሎት ለመቀየር ለጀማሪ ኩባንያዎች የአቅም ግንባታና የሥራ ዕድገት ድጋፍ በመስጠት የሀገሪቱን የፈጠራ ሥነ-ምኅዳር ለማጠናከር እንደሚሰራ አመላክተዋል።

በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ስታርታፖች በጸደቀው የስታርታፕ አዋጅ መሠረት የሚገባቸውን ድጋፍ በማግኘት ሥራዎቻቸውን እንዲያፋጥኑ የሚደረግ መሆኑን ሚኒስትሯ አመልክተዋል። በአጠቃላይ የዳታ ማዕከሉ የመሠረተ ልማት ድጋፍ ሲሰጥ፣ ኢኖቢዝ-ኬ ደግሞ የፈጠራ ሐሳቦችን ወደ ኢኮኖሚያዊ ውጤት በመቀየር የ«ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» ራዕይን እውን ለማድረግ ወሳኝ አቅም እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።

#MInT#BETIn #BioTechnology #Innovation #DigitalEthiopia

Ethiopian Communications Authority

Space science and geo-spatial institute

Ethiopian Technology Authority

Ethiopian Intellectual Property Authority/EIPA የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን

 

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251111265737
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2026 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ