+251111265737
contact@mint.gov.et
ክብርት ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ የአእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ከምዝገባ ባሻገር ፈጠራን እንዲያበረታታና ወደ ኢኮኖሚያዊ እሴት እንዲቀይር አቅጣጫ ሰጡ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ባደረጉት ጉብኝት፣ ባለሥልጣኑ ከምዝገባ ባሻገር ፈጠራን፣ የፈጠራ ግኝቶችንና የምርምር ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ መፍትሔዎች፣ ኢኮኖሚያዊ እሴትና ሕዝባዊ ጥቅም ለመቀየር ማገዝ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ክብርት ሚኒስትሯ በፈጠራ ባለቤቶች፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በኢንዱስትሪ፣ በባለሀብቶችና በፋይናንስ ተቋማት መካከል ያለው አጋርነት እንዲጠናከር፣ ለፈጠራ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያመቻቹ የሕግ ማዕቀፎች እንዲዘረጉ፣ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በዲጂታል መንገድ እንዲሰጡና የኢትዮጵያ ብራንዶች አስተማማኝ የህግ ከለላና ጥበቃ እንዲያገኙ አቅጣጫ ሰጥተዋል። የዜጎችን የፈጠራ ችሎታና ነጻ የፈጠራ አስተሳሰብ እያጎለበቱ፣ ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘመን ዝግጁ መሆን እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ክብርት ሚኒስትሯ ስኬት ከውጤታማ ምዝገባና የመብት ጥበቃ ጎን ለጎን፣ በተግባር በዋሉ ፈጠራዎች፣ በተገኘ የምርታማነት ዕድገትና እንዲፈጠሩ በተመቻቹ የሥራ ዕድሎች መለካት እንዳለበት አሳስበዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251111265737
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች