+251111265737

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ክብርት ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን ዜጎችን፣ ንብረትንና አካባቢን በመጠበቅ ለሀገራዊ ልማት ሊለካ የሚችል አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ሰጡ

ክብርት ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ፣ ከሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታዎችና ከተጠሪ ተቋማት ዋና ዳይሬክተሮች ጋር ባደረጉት የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን ጉብኝት፣ ተቋሙ ሕጋዊ ተልዕኮውን በማጥራትና ተቋማዊ አቅሙን በማጠናከር ለደህንነቱ የተጠበቀ የቴክኖሎጂ ልማትና አጠቃቀም ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥር አሳስበዋል።

ክብርት ሚኒስትሯ ከሌሎች ተቆጣጣሪ አካላት ጋር ኃላፊነቶችን በግልጽ መለየት፣ የሕግ ማዕቀፎችንና የላብራቶሪ አቅምን ማጠናከር፣ የሕዝብ ግንዛቤን ማሳደግና አገልግሎቶችን በዲጂታል ተደራሽ ማድረግ ላይ ትኩረት እንዲደረግ ጠቁመዋል።

የቁጥጥር ሥራ ስኬት በፈቃድና በምርመራ ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በተቀነሱ አደጋዎች፣ በተጠበቀ ደህንነትና ለፈጠራና ለሀገራዊ ልማት በተበረከተ ተጨባጭ አስተዋጽኦ መለካት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

#የኢትዮጵያቴክኖሎጂባለሥልጣን #ቴክኖሎጂ #የሕዝብደህንነት #ፈጠራ #ዲጂታልኢትዮጵያ

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251111265737
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2026 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ