+251118132191
contact@mint.gov.et
ዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሴልስፎርስ (Salesforce) በኢትዮጵያ ስራ ለመጀመር ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የቴክኖሎጂ ትብብርን ለማጠናከር ከድርጅቱ የቀጠናዊ ምክትል ፕሬዝዳንት Mr. Omar Oualif እና የልዑካን ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ እና በ Salesforce መካከል ግንባር ቀደም የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር (CRM) መድረክ አማካኝነት በጠንካራ ዓለም አቀፍ መገኘት መካከል የትብብር መስኮችን በመዳሰስ በአቅም ግንባታ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት ዝርጋታ እና በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ ትብብርና ፈጠራን በማጎልበት ዙሪያ ያተኮረ ነበር።
በውይይቱ ላይ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ስራ ለመጀመር ያሳየውን ፍላጎት አድንቀው ሚኒስቴር መስሪያቤታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
በኢትዮጵያ ጠንካራ የሆነ ዲጂታል ስነ-ምህዳር ለመገንባት እንደ Salesforce ካሉ አለምአቀፍ ኩባንያዎች ጋር ለመስራት ዝግጁ ነን ያሉት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ዲጂታል 2030 ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂን እውን ለማድረግ አስተዋጻኦ ከሚያደጉ የግል ኩባኛዎች አንዱ እንደሚሆንም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም በኢትዮጵያ ለቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጥሩ ከባቢያዊ ሁኔታ እየተፈጠር መሆኑን ገልጸው በዚህ እድል ሌሎች መሰል የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በዘርፉ በሃገራችን መዋለ ንዋያቸውን በማፍሰስ እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
መሰረቱን በአሜሪካ ያደረገው ይህ ሴልስፎርስ (Salesforce ) የቴክኖሎጂ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክም አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ጠንካራ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት እና የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በመንግስት የተሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አብራርተዋል።
የዲጂታል መሠረተ ልማትን ለመገንባት ከፍተኛ ኢንቨስትመንቶች ተደርገዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፈ ደረጃ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን ኢያስመዘገበች ባለው ውጤት በትላልቅ የዘርፉ ተዋናይ በሆኑ ኩባንያዎችን ተመራጭ እንድትሆን አስችሏቷል ብለዋል።
የ Salesforce ቀጠናዊ ምክትል ፕሬዝዳንት Mr. Omar Oualif Salesforce ድርጅቱ የ26 አመት ልምድ እንዳለው ገልጸው ፤ በክላውድ ላይ የተመሰረተ የሶፍትዌር ኩባንያ መሆኑን ጠቅሰው።
በቅርቡ በአዲስ አበባ ቢሮ በመክፈት በሽያጭ፣ በደንበኞች አገልግሎት፣ በገበያ አውቶሜሽን፣ በኢ-ኮሜርስ፣ መረጃን በመተንተን፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በመተግበሪያ ልማት ላይ ያተኮሩ ስራዎችን እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች