+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

በኒጀር የኮሚኒኬሽንና አዲስ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር የተመራው ልዑክ የኢትዮጵያን ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ጎበኙ፣

ክቡር አጂ አሊ የኮሚኒኬሽንና አዲስ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣ ሚ/ር አብዱ ኢብራሂም የህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር፣ ሚ/ር አህመድ ኢብራሂም የብሄራዊ መታወቂያ ዲጂታላዜሽን ዳይሬክተር እና ሚ/ር መሃመዱ ማማን ተቀዳሚ የኒጀር ኢንባሲ ፀሃፊ ዛሬ ግንቦት 14፣ 2017 ዓ.ም. በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ ግብዣ መነሻነት በኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ያሉ ኮሜርሻል ዳታ ሴንተሮችን (ራክሲዎ ኢትዮጵያና ዊንጉ አፍሪካ) ጨምሮ በሶፍትዌር ልማት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግና በስልጠና የተሰማሩ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገር ኩባንያዎችን ጎብኝተዋል።

ክቡር አጂ አሊ በጉብኝታቸው ወቅት የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አድንቀው በሁሉም የዲጂታል ዘርፍ እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች እያመጡ ያሉት ውጤቶች በግልፅ የሚታዩ ናቸው ብለዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፈጣን የዲጂታል ጉዞና ስኬት ለአፍሪካ ሃገራት የሚሰጠው ልምድ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ሃገራቸው ኒጀርና የሳህል አካባቢም በዘርፉ ትብብራቸውን ከኢትዮጵያ ጋር እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ