+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ዘመኑን በሚዋጁ ቴክኖሎጂዎች ላይ የሚደረጉ የሀካቶን(Hackathon) ውድድሮችን በማጎልበት ተሻጋሪ የሆኑ አቅሞች መፈጠር እንዳለባቸው ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ገለፁ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲና የኢትዮጵያ ወጣቶች ስራ ፈጠራ ማህበር ከአለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) ጋር በመተባበር የሀካቶን(Hackathon) ውድድር አካሄዱ።

በመክፈቻ ፕሮግራሙ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የሀገራችን ኢኮኖሚ ዋልታና ማገር የሆነውን የግብርናውን ዘርፍ በአርተፊሻል ኢንተለጀንስን(AI) ቴክኖሎጂ በማዘመን የምግብ ስርዓታችንን ለማጎልበት በሚያስችሉ የሀካቶን ውድድሮች ላይ በትብብር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ይበልጥ ሊጠናከሩ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ህይወት ሁሉ ቴክኖሎጂ የሆነበት አለም ላይ ውድድሮች የእድገት መሰረት ናቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በሀገራችን ያለውን የስራ እድል ለማስፋትና በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማጎልበት የሀካቶን (Hackathon) ውድድር ወሳኝ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።

ምቹ ስነምህዳርን የሚፈጥር የስታርታፕ አዋጅ መፅደቁን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው ለሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት መሰረት ሊሆኑ የሚችሉ ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ለማበርከት ሁሉም ተዋናዮች አዋጁ የፈጠረውን ዕድል ተጠቅመው ተወዳዳሪ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብረሃም ደበበ ሀገራችን በዓለም ተወዳዳሪ የሆነ ቴክኖሎጂ ባለቤት መሆን የሚያስችላትን እድል ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት ለማሳካት የሀካቶን(Hackathon) ውድድሮችን ማስፋትና የዘርፉን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አንስተዋል።

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) ተወካይ አቶ ዳግላስ ማጉንዳ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚችሉ አርተፊሻል ኢንተለጀንስን(AI) የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በውድድር በማጎልበት ዘላቂ የግብርና ኢኮኖሚን ለመገንባት በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በተካሄደው የሀካቶን(Hackathon) ውድድር አሸናፊ የሚሆነው ቡድን በዓለም አቀፍ ደረጃ ልምድ ካላቸው ድርጅቶች የኢንኩቤሽን ፕሮግራም እና በሮም በሚካሄደው የሳይንስ ኢኖቬሽን ፎረም ላይ ኢትዮጵያን በመወከል የሚሳተፍ ይሆናል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ