+251118132191
contact@mint.gov.et
የሀገራችንን ኢኮኖሚ በአጭር ጊዜ ለማሳደግና በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ተቋማትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማዘመን እንደሚገባ ተገለፀ።
በሚኒስተር መስሪያ ቤቱ የለማውን የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የኤሌክትሮኒክ ሰርቪስ አገልግሎት ስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የብሔራዊ ኤሌክትሮኒክስ መንግስት ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ የተከበሩ ወ/ሮ ሚራጅ ዘኪይ በተቋማት እየተሰጡ ያሉ መንግስታዊ አገልግሎቶችን ማዘመን በ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ላይ ከተቀመጡት ግቦች አንዱ መሆኑን ገልፀው የመንገስት አገልግሎቶችን ማዘመን፣ ከሰው እጅ ንክክ ነፃ ማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግርን የሚቀርፍና ዜጎች ያለ ድካምና ያለ እንግልት ቀልጣፋ አገልግሎቶችን በቀላሉ ካሉበት ቦታ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል።
አክለውም ዲጂታል ኢትዮጵያን 2025 አውን ለማድረግ ተቋማት አሠራሮቻቸውን እያዘመኑ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎት መስጠት ግዴታም መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳሉ ሞሲሳ በበኩላቸው ለምንሰጣቸው አገልግሎቶች ማዘመንና ከዓለም ቴክኖሎጂው ዕድገት ጋር አብረን ለመሄድ የግድ መሆኑን ገልፀዋል።
የምንሰጣተቸው አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ እንዲሆኑ አዳዲስ የዲጂታል ሲሰተሞችን በማበልፀግና የባለሙያዎቻችን አቅም በመገንባት ከቴክኖሎጂ አበልፃጊ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
ዓለም ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ሥርዓት እየተሸጋገረ ባለበት ወቅት ከቴክኖሎጂው ዕድገት ጋር አብሮ ለመሄድ የሚደርገው ጥረትና የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን አሟልቶ ብቁና ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ እውቀት መታጠቅ እንዳለበት አሳስበዋል።
ተቋሙ በንግድ ምልክት (Trade Mark) እና ቅጅና የተዛማጅ መብቶች (Copy Right) የምዝገባ አገልግለሎት ዘርፎች የአንድ ማዕከል አገልግለሎቶችን ከመጪው ሐምሌ ወር 2017ዓ.ም ጀምሮ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው የሚፈልጉትን አገልግሎት መጠየቅና በተዘረጋው የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት ሲሰተም በማመልከት መገልግል እንደሚጀምሩ አሳውቋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች