+251118132191
contact@mint.gov.et
የሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ የሰው ሀብት ልማት ላይ መስራት ወሳኝ ሚና እንዳለው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ገለፁ፡፡
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቪስኪ ኢንኩቤሽን ማዕከል/Innobiz-K Ethiopia/ በአይሲቲ፣ አግሪ-ቴክ፣ ፊን-ቴክ ኢ-ኮሜርስ፣ ጤና-ቴክ፣ ቱሪዝም-ቴክ እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ እየሰሩ ላሉ ለ24 ፖስት ኸርሊ ስቴጅ ስታርታፖች (ድርጅቶች) ለሶስት ተከታታይ ቀናት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ከፍተኛ የሰው ሀብት ያላት ሀገራችን እንድትበለፅግ የወጣቱን ሀይል ላይ የአቅም ግንባታ ስራን በመስራት የኢኮኖሚ እድገታችንን ማፋጠን እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡
የሀገራችን ወጣቶች ለመለወጥና የሀብት ባለቤት መሆን ከፈለጉ እራሳቸውን በማብቃት ስራን ሳይመርጡ ዝቅ ብለው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በኢኖቪስኪ ኢንኩቤሽን ማዕከል /Innobiz-K Ethiopia/ መሰልጠን መታደል ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በቅርብ ጊዜ በተቋማችን የሰለጠኑ ጀማሪ ስታርታፖች ዛሬ የሀብት ባለቤት ከመሆንም አልፈው በቀን ከፍተኛ ገቢ በማስገባት እራሳቸውንና ሀገራቸውን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
ለድርጅቶቹ የተሰጠው ስልጠና በኢትዮጵያ የኢኖቬሽን ስነምህዳር፣ በደንበኛ አያያዝ፣ በሀብት አስተዳደር፣ በገበያ ጥናት፣ በአመራርና ግጭት አፈታት፣ በተግባቦትና አቀራረብ ችሎታ፣ በኢቨስትመንት ዝግጅትና ሌሎች አቅም ሊፈጥሩ በሚችሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መሰረት ያደረጉ ናቸው፡፡
ስልጠናውን ወስደው ላጠናቀቁ ድርጅቶች ምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ሲሆን በቀጣይ ከ24 ድርጅቶች 12 በመምረጥ ለአምስት ወራት ድጋፍ ሰጪ አሰልጣኞች ተመድቦላቸው በየተቋማቸው በመሄድ እገዛ እንደሚደረግላቸው ተጠቁሟል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች